የርዕስ ማውጫ
የካቲት 15, 2008
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት:-
መጋቢት 17-23
ገጽ 3
የሚዘመሩት መዝሙሮች:- 16 (37), 9 (26)
መጋቢት 24-30
ገጽ 7
የሚዘመሩት መዝሙሮች:- 58 (138), 27 (57)
መጋቢት 31–ሚያዝያ 6
ገጽ 12
የሚዘመሩት መዝሙሮች:- 76 (172), 33 (72)
ሚያዝያ 7-13
ገጽ 16
የሚዘመሩት መዝሙሮች:- 93 (211), 92 (209)
ሚያዝያ 14-20
ገጽ 21
የሚዘመሩት መዝሙሮች:- 74 (168), 8 (21)
የጥናት ርዕሶች ዓላማ
የጥናት ርዕሶች 1, 2 ገጽ 3-11
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው በሚገኙ ታሪኮች ላይ ማሰላሰል እምነታችንን ያጠነክርልናል። ይሖዋን ዘወትር በፊታችን የምናደርግ ከሆነ ለጸሎታችን መልስ ይሰጠናል። ይሁንና ስለ ይሖዋ ዘወትር ማሰብ እንድንችል እሱን መታዘዝና ምንጊዜም በእሱ መታመን አለብን። በይሖዋ መንገድ መሄድ እምነት የሚጣልብን፣ ትሑት፣ ደፋርና ለሌሎች የምናስብ ሰዎች እንድንሆን ያደርገናል።
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ገጽ 12-20
ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ ሚስዮናዊ ነበር። በእነዚህ የጥናት ርዕሶች ውስጥ ኢየሱስ ሥልጠና ያገኘው እንዴት እንደነበር እንዲሁም ስላስተማረበት መንገድና በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ስላደረጉት ባሕርያት እንመለከታለን። የኢየሱስን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት እንደሆነና ምሥራቹን የምናውጅላቸውን ሰዎች ልብ በሚነካ መንገድ እንዴት ማስተማር እንደምንችልም እንመረምራለን።
የጥናት ርዕስ 5 ገጽ 21-25
በዚህ ርዕስ ውስጥ፣ የክርስቶስ መገኘት ረዘም ያለ ጊዜን ያመለክታል ሊባል የሚችለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን። እንዲሁም ኢየሱስ የተጠቀመበት “ይህ ትውልድ” የሚለው አገላለጽ እነማንን እንደሚያመለክት ለማስረዳት የቀረቡትን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎች እንመረምራለን። (ማቴ. 24:34) በተጨማሪም “ይህ ትውልድ” የሚቆይበትን የጊዜ ርዝመት ማስላት የማይቻለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ:-
እስራኤላውያን ከፈጸሙት ስሕተት ትምህርት ማግኘት
ገጽ 26
የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የማርቆስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
ገጽ 28
የጊልያድ ምሩቃን “መቆፈር እንዲጀምሩ” ማበረታቻ ተሰጣቸው
ገጽ 31