የርዕስ ማውጫ
ሚያዝያ 15, 2010
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ከግንቦት 31, 2010–ሰኔ 6, 2010
እናንት ወጣቶች—ይሖዋን ለማገልገል ያላችሁ ፍላጎት እያደገ ይሂድ
ገጽ 3
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 11, 41
ከሰኔ 7-13, 2010
መንፈስ ቅዱስ የይሖዋን ዓላማ በማስፈጸም ረገድ የሚጫወተው ሚና
ገጽ 7
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 43, 19
ከሰኔ 14-20, 2010
ገጽ 20
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 29, 52
ከሰኔ 21-27, 2010
ገጽ 24
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 54, 17
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 3-7
ይሖዋ የእሱን መመሪያ እንዲሰሙ፣ እንዲማሩና እንዲከተሉ ወጣቶችን ጋብዟቸዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፣ ጸሎትና መልካም ምግባር ወጣቶች ይሖዋን በሙሉ ልባቸው እንዲያመልኩት የሚረዷቸው እንዴት እንደሆነ በዚህ የጥናት ርዕስ ላይ ይብራራል።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 7-11
የይሖዋ ዓላማ ሙሉ በሙሉ ፍጻሜውን እንዳያገኝ የሚያግደው ነገር እንደሌለ እናውቃለን። ይህ የጥናት ርዕስ መንፈስ ቅዱስ የይሖዋን ዓላማ በማስፈጸም ረገድ ጥንት ምን ሚና እንደተጫወተ እንዲሁም አሁንና ወደፊት ምን ድርሻ እንደሚኖረው ያብራራል።
የጥናት ርዕስ 3 ከገጽ 20-24
የሰይጣን ዓለም መጥፊያው እየተቃረበ ሲመጣ ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና የሚያበላሹ ምስሎችን የያዙ ነገሮች ከመቼው ጊዜ ይበልጥ እየተዥጎደጎዱብን ነው። በዚህ የጥናት ርዕስ ላይ ከእነዚህ ነገሮች አንዳንዶቹን እንመለከታለን፤ እንዲሁም ሰይጣን በእነዚህ ነገሮች የሚጠቀመው ለምን እንደሆነና ራሳችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።
የጥናት ርዕስ 4 ከገጽ 24-28
ለአምላክ አገልግሎት ያለንን ቅንዓት ይዘን ለመቀጠል ምን ሊረዳን ይችላል? ክርስቶስን መከተላችንን መቀጠል ከፈለግን የትኛውን ዝንባሌ እንዳናዳብር ልንጠነቀቅ ይገባል? ይህ የጥናት ርዕስ ለእነዚህ አስፈላጊ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ፦
ታስታውሳለህ? 12
መከራዎችን በጽናት መቋቋማችን በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት አጠናክሮልናል 16