የርዕስ ማውጫ
ግንቦት 15, 2010
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ሰኔ 28, 2010–ሐምሌ 4, 2010
እናንት ወንዶች፣ ለክርስቶስ ራስነት ትገዛላችሁ?
ገጽ 8
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 5, 42
ሐምሌ 5-11, 2010
እናንት ሴቶች፣ ለራስነት ሥልጣን መገዛት ያለባችሁ ለምንድን ነው?
ገጽ 12
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 3, 6
ሐምሌ 12-18, 2010
ወንድሞች፣ ለመንፈስ ብላችሁ በመዝራት ለኃላፊነት ለመብቃት ተጣጣሩ!
ገጽ 24
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 45, 11
ሐምሌ 19-25, 2010
ገጽ 28
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 38, 26
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕሶች 1, 2 ከገጽ 8-17
የመጀመሪያው የጥናት ርዕስ ወንዶች፣ ራሳቸው ለሆነው ለክርስቶስ መገዛታቸውና ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ረገድ የእሱን ምሳሌ መከተላቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያሳያል። ሁለተኛው የጥናት ርዕስ ደግሞ ክርስቲያን ሴቶች ‘የሴት ሁሉ ራስ ወንድ ነው’ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ እንዴት ሊመለከቱት እንደሚገባ ያብራራል።
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ከገጽ 24-32
በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ለሌሎች መሥዋዕትነት መክፈል የሚለው ሐሳብ እምብዛም አይዋጥላቸውም። የመጀመሪያው የጥናት ርዕስ፣ በተለይ የተጠመቁ ወንድሞች መሥዋዕትነት ስለ መክፈልና የጉባኤ አገልጋይ ወይም ሽማግሌ በመሆን ኃላፊነት ስለ መሸከም ያላቸውን አመለካከት እንዲመረምሩ ለመርዳት ተብሎ የተዘጋጀ ነው። ሁለተኛው የጥናት ርዕስ የአምላክን ቅዱስ መንፈስ ላለማሳዘን ምን ማድረግ እንደምንችል ያብራራል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ፦
የታመመ የቤተሰብ አባልን ስትንከባከብ መንፈሳዊነትህን ጠብቅ 17
ካራን—ሞቅ ያለ እንቅስቃሴ የነበራት ጥንታዊት ከተማ 20