የርዕስ ማውጫ
የካቲት 15, 2011
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ከሚያዝያ 4-10, 2011
መንፈስ ቅዱስ—በፍጥረት ሥራ ላይ የነበረው ድርሻ!
ገጽ 6
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 15, 2
ከሚያዝያ 11-17, 2011
የአምላክን ሞገስ ማግኘት ወደ ዘላለም ሕይወት ይመራል
ገጽ 13
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 27, 51
ከሚያዝያ 18-24, 2011
ገጽ 24
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 22, 40
ከሚያዝያ 25, 2011–ግንቦት 1, 2011
ገጽ 28
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 29, 6
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 6-10
በዚህ የጥናት ርዕስ ውስጥ የቀረቡት ነጥቦች አምላክ ሰማይንና ምድርን ለመፍጠር ቅዱስ መንፈሱን እንዴት እንደተጠቀመበት ያለንን ግንዛቤ ያሰፉልናል። ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ ጥበበኛና ከሁሉ በላይ ኃያል የሆነ ፈጣሪያችን ስለ መሆኑ ያለንን እምነት ያጠናክሩልናል።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 13-17
በጥቅሉ ሲታይ ሰዎች በአብዛኛው የሚያሳስባቸው በቁሳዊ ረገድ የተደላደለ ሕይወት መምራት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ይበልጥ ሊያሳስበን የሚገባው የአምላክን ሞገስ ማግኘታችን እንደሆነ ይገልጻል። ይህ የጥናት ርዕስ በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት የማጠናከርን አስፈላጊነት ያጎላል፤ እንዲሁም የእሱን ሞገስ ለማግኘት ምን እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብን ይገልጻል።
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ከገጽ 24-32
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር “ጽድቅን ወደድክ፣ ዓመፅን ጠላህ” ይላል። (ዕብ. 1:9) እነዚህ የጥናት ርዕሶች ኢየሱስን መምሰል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራሉ። እንዲሁም ለጽድቅ ፍቅር ማዳበራችንና ዓመፅን መጥላታችን አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ይገልጻሉ።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ