የርዕስ ማውጫ
መጋቢት 15, 2011
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ከግንቦት 2-8, 2011
የዓለምን መንፈስ ሳይሆን የአምላክን መንፈስ ተቀበሉ
ገጽ 8
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 23, 38
ከግንቦት 9-15, 2011
ገጽ 12
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 43, 48
ከግንቦት 16-22, 2011
ገጽ 24
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 54, 24
ከግንቦት 23-29, 2011
ገጽ 28
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 32, 43
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 8-12
በዙሪያችን ያሉ ሰዎች የዓለምን መንፈስ ያንጸባርቃሉ፤ ታዲያ እኛ ከእነሱ የተለየን መሆን እንችላለን? ይህ የጥናት ርዕስ የዓለም መንፈስ በእኛ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችለው እንዴት እንደሆነ ለመገንዘብ ይረዳናል። የአምላክን መንፈስ መቀበልን በተመለከተ ከኢየሱስ ምን ልንማር እንደምንችልም እንመለከታለን።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 12-16
በይሖዋ መታመን ሲባል ምን ማለት ነው? ከዚህ የጥናት ርዕስ እንደምንመለከተው በአምላክ መታመን፣ ስለ አዲሱ ዓለም በሰጠን ተስፋ ከማመን የበለጠ ነገርን ይጨምራል። የአምላክን መንገዶችና መሥፈርቶች በሙሉ ልብ መቀበልንና ከዓለም መንገዶች መራቅን ያካትታል።
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ከገጽ 24-32
እነዚህ ርዕሶች ኖኅና ቤተሰቡ፣ ሙሴ እንዲሁም ኤርምያስ የተሰጣቸውን ተልእኮ ለመወጣት ምንጊዜም ዝግጁ የነበሩት እንዴት እንደሆነ ያብራራሉ፤ እንዲሁም አምላክ የገባው ቃል ሲፈጸም የሚመለከቱት እንዴት እንደሆነ ያሳያሉ። ከእነዚህ ሰዎችም ሆነ ከነበራቸው አመለካከት ምን ትምህርት ማግኘት እንደምንችል ለማስተዋል ሞክር።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
3 የውሸት ምክንያት እያቀረባችሁ ራሳችሁን አታታልሉ
20 የእምነት ባልንጀሮቻችሁን ፈጽሞ ችላ አትበሉ