የርዕስ ማውጫ
ሚያዝያ 15, 2011
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ከግንቦት 30, 2011–ሰኔ 5, 2011
ለይሖዋ የምናቀርበውን አገልግሎት በቁም ነገር ተመልከቱት
ገጽ 9
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 43, 10
ከሰኔ 6-12, 2011
ገጽ 13
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 2, 9
ከሰኔ 13-19, 2011
ገጽ 18
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 25, 11
ከሰኔ 20-26, 2011
ገጽ 23
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 6, 48
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 9-13
ብዙዎች ኃላፊነታቸውን እንደዋዛ በሚመለከቱበት በዚህ ዓለም ውስጥ ክርስቲያኖች ነገሮችን በቁም ነገር መመልከት ይኖርባቸዋል። በተለይ ለይሖዋ ከምናቀርበው አምልኮ ጋር በተያያዘ እንዲህ ያለውን ባሕርይ ማዳበራችን በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ርዕስ ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን ምን ያህል በቁም ነገር መመልከት እንዳለብን ለመረዳት የሚያስችሉን ሚዛናዊና ቅዱስ ጽሑፋዊ ሐሳቦችን ይዟል።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 13-17
ብዙ ሰዎች ውሳኔ ለማድረግ ይቸገራሉ። ጥሩ ውሳኔ እንዴት ማድረግ እንደምንችል ማወቃችን አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት በዚህ ርዕስ ውስጥ እንመረምራለን። በተጨማሪም የምናደርገው ውሳኔ አምላክን የሚያስከብር እንዲሆን ልንወስዳቸው የምንችላቸው ጠቃሚ እርምጃዎች ይብራራሉ።
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ከገጽ 18-27
“የመንፈስ ፍሬ” ምንድን ነው? ይህን ፍሬ ማፍራት የምንችለው እንዴት ነው? የመንፈስ ፍሬን ማፍራት ያለብን ለምንድን ነው? ዘጠኙን የመንፈስ ፍሬ ገጽታዎች ስንመረምር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ታገኛለህ። እነዚህ ርዕሶች ብዙዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ሐሳቦችንም ይዘዋል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
3 አምላክ እንደሚመራን የሚያሳየውን ማስረጃ ታስተውላለህ?
6 ሐቀኝነት በጎደለው ዓለም ውስጥ ሐቀኛ ሆኖ መኖር
28 ታስታውሳለህ?