የርዕስ ማውጫ
ግንቦት 15, 2011
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ሰኔ 27, 2011–ሐምሌ 3, 2011
ገጽ 7
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 11, 22
ሐምሌ 4-10, 2011
ገጽ 11
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 32, 18
ሐምሌ 11-17, 2011
በሕይወትህ ውስጥ ከሁሉ የላቀውን ቦታ የምትሰጠው ለማን ነው?
ገጽ 16
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 51, 49
ሐምሌ 18-24, 2011
ገጽ 21
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 1, 43
ሐምሌ 25-31, 2011
በይሖዋ ሙሉ በሙሉ መታመን የደኅንነት ስሜት እንዲያድርብን ያደርጋል
ገጽ 28
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 46, 23
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕሶች 1, 2 ከገጽ 7-15
የመጀመሪያው የጥናት ርዕስ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በመንፈሳዊ ንቁ በመሆን ረገድ ያለበትን ኃላፊነት ያብራራል። ሁለተኛው የጥናት ርዕስ ቤተሰቦች ዓይናቸው ምንጊዜም አጥርቶ የሚያይ እንዲሆን ማድረጋቸው፣ መንፈሳዊ ግቦች ላይ ለመድረስ መጣራቸው እንዲሁም የቤተሰብ አምልኮ የሚያደርጉበት ቋሚ ምሽት እንዲኖር ማድረጋቸው ለመላው ቤተሰብ መንፈሳዊ ደኅንነት አስተዋጽኦ የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
የጥናት ርዕስ 3 ከገጽ 16-20
የአምላክ አገልጋዮች በሕይወታቸው ውስጥ ከሁሉ የላቀውን ቦታ ሊሰጡ የሚገባው ለይሖዋ ነው። ይህን በተመለከተ የመጀመሪያዋ ሴት ሔዋን፣ ታማኙ ኢዮብና ፍጹም የሆነው የአምላክ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ካጋጠማቸው ነገር ምን ትምህርት እንደምናገኝ በዚህ የጥናት ርዕስ ላይ እንመለከታለን።
የጥናት ርዕስ 4 ከገጽ 21-25
በሮም ምዕራፍ 11 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ አንድ ምሳሌያዊ የወይራ ዛፍ ተናግሯል። የዛፉ የተለያዩ ክፍሎች ምን ያመለክታሉ? የዛፉ ክፍሎች ምን ትርጉም እንዳላቸው በዚህ ርዕስ ውስጥ ስንመረምር ስለ ይሖዋ ዓላማ ይበልጥ ማወቅ እንችላለን፤ እንዲሁም በጥበቡ ጥልቀት እንደመማለን።
የጥናት ርዕስ 5 ከገጽ 28-32
በዚህ የጥናት ርዕስ ላይ ንጉሥ ዳዊት ያቀናበራቸውን መዝሙር 3ን እና 4ን እንመረምራለን። በመንፈስ መሪነት የተጻፉት እነዚህ መዝሙሮች ይሖዋ እንዲረዳን ወደ እሱ የምንጸልይና በእሱ ላይ ሙሉ በሙሉ የምንታመን ከሆነ የደኅንነት ስሜት ሊያድርብን እንደሚችል ያሳያሉ። ዳዊት መከራዎች ባጋጠሙት ወቅት፣ ለምሳሌ ልጁ አቤሴሎም በከዳው ጊዜ እንዲህ አድርጓል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
26 ፍጹም መሪያችን የሆነውን ክርስቶስን መከተል