የርዕስ ማውጫ
ኅዳር 15, 2011
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ከታኅሣሥ 26, 2011–ጥር 1, 2012
ገጽ 6
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 49, 23
ከጥር 2-8, 2012
ሕይወትንና ሰላምን እንድታገኙ እንደ መንፈስ ፈቃድ ተመላለሱ
ገጽ 10
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 52, 6
ከጥር 9-15, 2012
በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ “ጊዜያዊ ነዋሪ” ሆኖ መኖር
ገጽ 16
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 40, 26
ከጥር 16-22, 2012
ገጽ 24
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 42, 1
ከጥር 23-29, 2012
ገጽ 28
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 45, 10
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 6-10
አምላክ በሰጠን የጸሎት መብት በሚገባ እየተጠቀምክ ነው? የሚያስጨንቁ ሁኔታዎችና ውሳኔ የሚያሻቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙህ እንዲሁም ፈተናዎችን ለመቋቋም ስትታገል ጸሎት ሊረዳህ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ከዚህ የጥናት ርዕስ ትምህርት ታገኛለህ።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 10-14
በሮም የሚገኙ ክርስቲያኖች፣ ሕይወትና ሰላም ማግኘት ከፈለጉ አእምሯቸው በምን ነገር ላይ ማተኮር እንዳለበት ሐዋርያው ጳውሎስ ነግሯቸዋል። ጳውሎስ ለእነዚህ ክርስቲያኖች ከሰጠው ምክር ምን ጥቅም ማግኘት እንደምትችል ከዚህ የጥናት ርዕስ ጥሩ ግንዛቤ ታገኛለህ።
የጥናት ርዕስ 3 ከገጽ 16-20
በዚህ የጥናት ርዕስ ላይ እንደተገለጸው የጥንቶቹ ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች እንደ “ጊዜያዊ ነዋሪዎች” ሆነው ኖረዋል። የጥንቶቹ የኢየሱስ ተከታዮችም ቢሆኑ የኖሩት በዚህ መልክ ነው። ይሁንና በዛሬው ጊዜ ስላሉት እውነተኛ ክርስቲያኖችስ ምን ማለት ይቻላል? በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ እንደ ጊዜያዊ ነዋሪ ሆኖ መኖር ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ከዚህ የጥናት ርዕስ ትምህርት ታገኛለህ።
የጥናት ርዕሶች 4, 5 ከገጽ 24-32
በአሁኑ ወቅት መንፈሳዊ ጉዳዮችን በበላይነት የሚከታተሉ ወንዶች በጣም ያስፈልጋሉ። ኢየሱስ በርካታ ወንዶች ምሥራቹን ተቀብለው ጉባኤውን ለማገልገል የሚያስችል ብቃት ላይ እንዲደርሱ ረድቷል። እኛም የእሱን ምሳሌ በመከተል በአገልግሎት ላይ የምናገኛቸውን ወንዶች እንዴት እንደምንረዳ እንዲሁም በጉባኤ ውስጥ የሚገኙ የተጠመቁ ወንዶች በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ባሉ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለማገልገል እንዲጣጣሩ መደገፍ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
15 “ለዘላለም የአካል ጉዳተኛ ሆኜ አልቀርም!”
22 ‘የልግስና ስጦታ ለመስጠት የሚያስችል መብት’ በማግኘትህ ደስተኛ ነህ?