የርዕስ ማውጫ
ታኅሣሥ 15, 2011
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶችና የሚጠኑበት ሳምንት፦
ከጥር 30, 2012–የካቲት 5, 2012
ጥሩ አርዓያም የማስጠንቀቂያ ምሳሌም ሊሆነን የሚችል ሰው
ገጽ 8
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 29, 22
ከየካቲት 6-12, 2012
በአምላክ መንፈስ መመራት ያለብን ለምንድን ነው?
ገጽ 13
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 38, 18
ከየካቲት 13-19, 2012
በአምላክ መንፈስ የተመሩ በጥንት ዘመን የነበሩ ታማኝ አገልጋዮች
ገጽ 18
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 54, 51
ከየካቲት 20-26, 2012
በአምላክ መንፈስ መመራት—በመጀመሪያው መቶ ዘመንና በዛሬው ጊዜ
ገጽ 22
የሚዘመሩት መዝሙሮች፦ 11, 31
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 8-12
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉ ሰዎች አሉ፤ ይሁን እንጂ ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ የማስጠንቀቂያ ምሳሌም ይሆኑናል። ከዚህ አንጻር የሰለሞንን ሕይወት በዚህ የጥናት ርዕስ ውስጥ እንመረምራለን። ታዲያ ከሰለሞን ታሪክ ለክርስትና ሕይወታችን የሚጠቅም ምን ትምህርት ማግኘት እንችል ይሆን?
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 13-17
በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በተሳካ ሁኔታ ሊመራን የሚችል አንድ ከፍተኛ ኃይል በአጽናፈ ዓለም ውስጥ አለ። ለመሆኑ ይህ ኃይል ምንድን ነው? በዚህ ኃይል መመራት የምንፈልገው ለምንድን ነው? ከዚህ ኃይል የተሟላ ጥቅም ለማግኘትስ ምን ማድረግ አለብን?
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ከገጽ 18-26
በጥንት ዘመን የነበሩ በርካታ የአምላክ አገልጋዮች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር። የአምላክ መንፈስ በእነሱ ላይ ይሠራ የነበረው እንዴት ነው? ይሖዋ እንዴት ይመራቸው እንደነበር ማጥናታችን የተሰጠንን ኃላፊነት ለመወጣት ትልቅ ማበረታቻ ይሆነናል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
3 ማስተካከያዎችን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን ይክሳል
31 ታስታውሳለህ?