የርዕስ ማውጫ
የካቲት 15, 2012
© 2012 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. የባለቤቱ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶች
ሚያዝያ 2-8, 2012
ገጽ 3 • መዝሙሮች፦ 14, 24
ሚያዝያ 9-15, 2012
ገጽ 10 • መዝሙሮች፦ 10, 47
ሚያዝያ 16-22, 2012
በጉባኤያችሁ ውስጥ ጥሩ መንፈስ እንዲሰፍን አድርጉ
ገጽ 18 • መዝሙሮች፦ 20, 28
ሚያዝያ 23-29, 2012
በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤት ውስጥ ደስታን ጠብቆ መኖር ይቻላል
ገጽ 26 • መዝሙሮች፦ 39, 6
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 3-7
ኢየሱስ ምንጊዜም ነቅተው እንዲጠብቁ ተከታዮቹን ያስጠነቀቃቸው ለምንድን ነው? ክርስቶስ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ነቅቶ እንደሚጠብቅ ያሳየባቸውን ሦስት መንገዶች እንዲሁም እኛ የእሱን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት እንደሆነ በዚህ ርዕስ ላይ እንመረምራለን።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 10-14
በጥንት ዘመን የይሖዋ አገልጋዮች ድፍረት ያሳዩት እንዴት እንደሆነ መመልከታችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል? ይህ ርዕስ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሰጠን ከመሆኑም በላይ ደፋሮች መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይጠቁመናል።
የጥናት ርዕስ 3 ከገጽ 18-22
ሁላችንም ብንሆን የራሳችን የሆነ የምናንጸባርቀው መንፈስ ወይም ተለይተን የምንታወቅበት ነገር አለን። በጉባኤ ውስጥ ጤናማና ጥሩ መንፈስ እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ በዚህ ርዕስ ላይ ይብራራል።
የጥናት ርዕስ 4 ከገጽ 26-30
በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች በየዕለቱ ብዙ ተፈታታኝ የሆኑ ነገሮች ይገጥሟቸዋል። ይህ ርዕስ ክርስቲያኖች በቤት ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ብሎም የማያምነው የቤተሰብ አባል እውነትን እንዲቀበል ነገሮችን ማመቻቸት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
15 ቅናት—አእምሯችንን ሊመርዝ የሚችል መጥፎ ባሕርይ
23 ናታን—ለንጹሕ አምልኮ በታማኝነት ጥብቅና የቆመ
31 ከታሪክ ማኅደራችን
ሽፋኑ፦ በኒው ዴልሂ፣ ሕንድ የሚገኙ ወንድሞች በቀን ውስጥ ከ300 በላይ ባቡሮችን በሚያስተናግደው የባቡር ጣቢያ ውስጥ ሆነው በአቅራቢያ ካሉ ከተሞች እየተመላለሱ ለሚሠሩ ሰዎችና ከአገሪቱ የተለያየ ክፍል ለሚመጡ መንገደኞች ሲመሠክሩ
ሕንድ
የሕዝብ ብዛት
1,224,614,000
አስፋፊዎች
33,182
የአስፋፊዎች ጭማሪ
5 በመቶ