የርዕስ ማውጫ
መጋቢት 15, 2012
© 2012 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. የባለቤቱ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶች
ሚያዝያ 30, 2012-ግንቦት 6, 2012
ገጽ 10 • መዝሙሮች፦ 32, 44
ግንቦት 7-13, 2012
ገጽ 15 • መዝሙሮች፦ 43, 47
ግንቦት 14-20, 2012
ገጽ 20 • መዝሙሮች፦ 54, 55
ግንቦት 21-27, 2012
ገጽ 25 • መዝሙሮች፦ 20, 17
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕሶች 1, 2 ከገጽ 10-19
የሐሰት ሃይማኖት ትምህርቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በመንፈሳዊ እንዲያንቀላፉ ወይም ድብታ እንዲይዛቸው አድርገዋል። እነዚህ ሁለት የጥናት ርዕሶች ሰዎችን እንዴት ከእንቅልፋቸው ማንቃት እንደምንችልና ይህን ማድረግ አጣዳፊ የሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራሉ። በተጨማሪም የጥድፊያ ስሜታችንን ጠብቀን መኖር የምንችለው እንዴት እንደሆነና በጥድፊያ ስሜት ማገልገል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ እንመረምራለን።
የጥናት ርዕስ 3 ከገጽ 20-24
ሐዋርያው ጴጥሮስ ቅቡዓን ክርስቲያኖች “ሕያው ተስፋ” እንዳላቸው ጽፏል። (1 ጴጥ. 1:3) ይህ ተስፋ የሚፈጸመው እንዴት ነው? የቅቡዓን ተስፋ መፈጸም “ሌሎች በጎች” ያላቸው ተስፋ ከመፈጸሙ ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው? (ዮሐ. 10:16) ይህ የጥናት ርዕስ በተስፋህ እንድትደሰት የሚያደርግህ ምክንያት ምን እንደሆነና ተስፋህ የሚፈጸምበትን ጊዜ በጉጉት መጠበቅ ያለብህ ለምን እንደሆነ ያብራራል።
የጥናት ርዕስ 4 ከገጽ 25-29
ኢየሱስ “የሎጥን ሚስት አስታውሱ” የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። (ሉቃስ 17:32) ኢየሱስ ይህን ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ምን ማለቱ ነበር? ኢየሱስ የሰጠውን ይህን ማስጠንቀቂያ በሥራ ላይ የምናውልባቸውን ሦስት መንገዶች እንድናስተውል የጥናት ርዕሱ ይረዳናል። አንተም በሕይወትህ ተግባራዊ ልታደርጋቸው የሚገቡ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ነጥቦች ታገኝ ይሆናል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
ሽፋኑ፦ በማላዊ የሚገኙ በርካታ ወጣት የይሖዋ ምሥክሮች የወጣቶች ጥያቄ ከተባለው መጽሐፍ ላይ አብረዋቸው ለሚማሩ ልጆች ትኩረት የሚስቡና ጠቃሚ ሐሳቦችን ያካፍላሉ
ማላዊ
የሕዝብ ብዛት
13,077,160
አስፋፊዎች
79,157
የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ
ከ1998 ወዲህ 1,031