የርዕስ ማውጫ
ሰኔ 15, 2012
© 2012 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. የባለቤቱ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶች
ሐምሌ 30, 2012–ነሐሴ 5, 2012
ገጽ 7 • መዝሙሮች፦ 37, 20
ነሐሴ 6-12, 2012
ይሖዋ “በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚገባቸውን ነገሮች” ይገልጣል
ገጽ 14 • መዝሙሮች፦ 43, 54
ነሐሴ 13-19, 2012
የይሖዋን አገልግሎት ማስቀደም ያለብን ለምንድን ነው?
ገጽ 20 • መዝሙሮች፦ 10, 45
ነሐሴ 20-26, 2012
ገጽ 25 • መዝሙሮች፦ 37, 1
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕሶች 1, 2 ከገጽ 7-18
ወደፊት በዓለማችን ላይ ስለሚከናወኑ ነገሮች ለማወቅ የሚያስችሉን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የትኞቹ ናቸው? እነዚህ ሁለት ርዕሶች በዳንኤል ምዕራፍ 2 ላይ ስለተጠቀሰው ግዙፉ ምስልና በራእይ ምዕራፍ 13 እና 17 ላይ ስለሚገኘው አውሬ ብሎም ስለ አውሬው ምስል የተነገሩትን ትንቢቶች ለመመርመር ይረዱናል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ የሚሰጠውን ማብራሪያ እንድትመለከት ተጋብዘሃል።
የጥናት ርዕስ 3 ከገጽ 20-24
አንድ ክርስቲያን ራሱን ወስኖ ሲጠመቅ በሕይወቱ ውስጥ የአምላክን ፈቃድ ለማስቀደም ቃል ገብቷል። በጥንት ዘመን የነበሩ ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች ባደረጓቸው ውሳኔዎች ላይ ማሰላሰላችን ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና ጥሪታችንን የምንጠቀምበትን መንገድ እንድንመረምር ያነሳሳናል።
የጥናት ርዕስ 4 ከገጽ 25-29
ይህ ርዕስ ነቢያትና የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ‘በመንፈስ ቅዱስ የተመሩት’ እንዴት እንደሆነ ጥሩ ግንዛቤ ይሰጠናል፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ምንጭ እንዳለው እርግጠኛ የምንሆንበትን ምክንያት ይጠቁማል። (2 ጴጥ. 1:21) በተጨማሪም ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለን አድናቆት እንዳይቀዘቅዝ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
30 “ጥበብ ያለበትን መመሪያ” በመሻት ጥበበኛ ሁኑ
ሽፋኑ፦ በተቻለ መጠን ለብዙ ሰዎች ምሥራቹን ለማዳረስ በተለያዩ ቦታዎችና ሁኔታዎች ላይ ለሚገኙ ሰዎች ምሥክርነቱ እየተሰጠ ነው። ከእነዚህ ቦታዎች መካከል አንዱ በፎቶው ላይ የሚታየውና በዳምንዮን ሳዱአ የሚገኘው ተንሳፋፊ የገበያ ስፍራ ነው።
ታይላንድ
የሕዝብ ብዛት
66,720,000
አስፋፊዎች
3,423
የዘወትር አቅኚዎች
824