የርዕስ ማውጫ
ጥቅምት 15, 2012
© 2012 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. የባለቤቱ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።
የጥናት እትም
የጥናት ርዕሶች
ከኅዳር 26, 2012–ታኅሣሥ 2, 2012
በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙንን መከራዎች በድፍረት መቋቋም
ገጽ 7 • መዝሙሮች፦ 54, 33
ከታኅሣሥ 3-9, 2012
ገጽ 12 • መዝሙሮች፦ 31, 50
ከታኅሣሥ 10-16, 2012
አምላክን በመታዘዝ በመሐላ ከገባው ቃል ተጠቃሚ ሁኑ
ገጽ 22 • መዝሙሮች፦ 54, 1
ከታኅሣሥ 17-23, 2012
ገጽ 27 • መዝሙሮች፦ 18, 43
የጥናት ርዕሶቹ ዓላማ
የጥናት ርዕስ 1 ከገጽ 7-11
የምንኖረው መከራ በሞላበት ዘመን ውስጥ ነው። ይህ ርዕስ በጥንት ጊዜም ሆነ በዘመናችን፣ የደረሰባቸውን ከባድ መከራ የተቋቋሙ ሰዎች ከተዉት ምሳሌ ትምህርት ማግኘት እንድንችል ይረዳናል። ከዚህም በተጨማሪ ምንም ነገር ቢመጣ ደፋር መሆንና አዎንታዊ አመለካከት መያዝ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንድንገነዘብ ያስችለናል።
የጥናት ርዕስ 2 ከገጽ 12-16
በዛሬው ጊዜ ያለው ዓለም በሚያንጽ ሳይሆን አፍራሽ በሆነ መንፈስ የተሞላ ነው። በዚህ የጥናት ርዕስ፣ በጉባኤው ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ አመለካከቶችንና ድርጊቶችን እንዴት ማስወገድ እንደምንችል እንዲሁም ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን የሚያስችል መንፈስ እንዴት ማዳበር እንደምንችል እንመለከታለን።
የጥናት ርዕሶች 3, 4 ከገጽ 22-31
የመጀመሪያው ርዕስ አምላክ ለመፈጸም የገባቸውን ክቡር መሐላዎች ያጎላል። ከገባው ቃል ጥቅም ለማግኘት አምላክን መታዘዝ እንዲሁም ቃላችንን መጠበቅ አለብን። ሁለተኛው የጥናት ርዕስ ደግሞ ቃላቸውን አክብረው የኖሩ ሰዎች የተዉልንን ምሳሌ ያጎላል፤ እንዲሁም የተጠመቁ ክርስቲያኖች “አዎ” ብለው የገቡትን የላቀ ክብደት የሚሰጠው ቃል አክብረው እንዲኖሩ ያበረታታል።—ማቴ. 5:37
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
17 ወዳጅነታችን 60 ዓመታት ቢያስቆጥርም ገና መጀመሩ ነው
ሽፋኑ፦ አቅኚ የሆኑ ባልና ሚስት በከተማዪቱ ውስጥ ሰው በብዛት በሚንቀሳቀስበት ቦታ ተንቀሳቃሽ የጽሑፍ መደርደሪያ ተጠቅመው ሲያገለግሉ
ታይምስ ስኩዌር፣ ማንሃተን፣ ኒው ዮርክ ሲቲ
600
አቅኚዎች በማንሃተን በሚገኙ
12
ቦታዎች ያገለግላሉ
55
በማንሃተን የሚገኙ ጉባኤዎች ቁጥር