የርዕስ ማውጫ
መጋቢት 15, 2013
© 2013 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. All rights reserved.
የጥናት እትም
ሚያዝያ 29, 2013-ግንቦት 5, 2013
ገጽ 3 • መዝሙሮች፦ 45, 32
ግንቦት 6-12, 2013
ገጽ 8 • መዝሙሮች፦ 31, 23
ግንቦት 13-19, 2013
ገጽ 13 • መዝሙሮች፦ 54, 24
ግንቦት 20-26, 2013
ገጽ 19 • መዝሙሮች፦ 51, 1
ግንቦት 27, 2013-ሰኔ 2, 2013
ገጽ 24 • መዝሙሮች፦ 27, 10
የጥናት ርዕሶች
▪ ይሖዋን የሚወዱ ‘ዕንቅፋት የለባቸውም’
ሁሉም ክርስቲያኖች የዘላለም ሕይወት ሽልማት ለማግኘት በሚደረገው ውድድር ላይ ናቸው። ይሁንና በወረስነው ኃጢአት ምክንያት ሁላችንም እንደናቀፋለን። ይህ የጥናት ርዕስ እንቅፋት ሊሆኑብን የሚችሉ አምስት ነገሮችን ለይተን ማወቅ እንድንችል የሚረዳን ከመሆኑም ሌላ እነዚህን እንቅፋቶች በመወጣት እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል ያብራራል።
▪ ይሖዋን “የሚያውቅ ልብ” አለህ?
የኤርምያስ መጽሐፍ ስለ ልብ የሚናገሩ በርካታ ሐሳቦችን ይዟል። ይህ ርዕስ ‘ያልተገረዘ ልብ’ ምን ማለት እንደሆነና እንዲህ ያለ ልብ ለክርስቲያኖችም እንኳ አደጋ ሊሆን የሚችለው እንዴት እንደሆነ እንድንገነዘብ ይረዳናል። በተጨማሪም ይሖዋን “የሚያውቅ ልብ” ሊኖረን የሚችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።—ኤር. 9:26፤ 24:7
▪ “አምላክን አውቃችኋል”—ከዚህ በኋላስ?
አምላክን ማወቅና በእሱ ዘንድ መታወቅ ምን እርምጃዎችን መውሰድ ይጠይቃል? አንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ ጉልምስና ላይ ከደረሰም በኋላ እድገት ማድረጉን መቀጠል ያለበት ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የሚችለውስ እንዴት ነው? ይህ ርዕስ የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ይረዳሃል።
▪ ይሖዋ መጠጊያችን ነው
ለእኛ ጥላቻ ባለው ዓለም ውስጥ የምንኖር ቢሆንም ፍርሃት ሊያድርብን አይገባም። ይህ ርዕስ ይሖዋ አምላክ ከሁሉ የላቀ አስተማማኝ መጠጊያ ሊሆንልን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
▪ የይሖዋን ታላቅ ስም አክብሩ
የአምላክን ስም ማወቅ ሲባል ምን ማለት ነው? በዚህ ስም መሄድ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አምላክ ስሙን የሚያቃልሉ ሰዎችን የሚመለከታቸው እንዴት ነው? ይህ ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
ሽፋኑ፦ ፊንላንድ ረጅም የባሕር ጠረፍ ያላትና በብዙ ደሴቶች የተከበበች አገር ናት። በተጨማሪም በተለይ በማዕከላዊና በምሥራቃዊ ፊንላንድ በሺህ የሚቆጠሩ ሐይቆች አሉ። የምሥራቹ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች ለተወሰነ ጊዜ ሄደው የሚያገለግሉ አንዳንድ አስፋፊዎች የስብከቱን ሥራ ለማከናወን በጀልባ ይጠቀማሉ
ፊንላንድ
የሕዝብ ብዛት፦
5,375,276
ሬሾ፦
1 የይሖዋ ምሥክር ለ283 ሰዎች
የዘወትር አቅኚዎች፦
1,824