የርዕስ ማውጫ
ጥቅምት 15, 2013
© 2013 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania. All rights reserved.
የጥናት እትም
ታኅሣሥ 2-8, 2013
ገጽ 7 • መዝሙሮች፦ 9, 15
ታኅሣሥ 9-15, 2013
ገጽ 12 • መዝሙሮች፦ 31, 25
ታኅሣሥ 16-22, 2013
ገጽ 21 • መዝሙሮች፦ 38, 6
ታኅሣሥ 23-29, 2013
ፍቅር ከተንጸባረቀበት የኢየሱስ ጸሎት ጋር ተስማምቶ መኖር
ገጽ 26 • መዝሙሮች፦ 22, 6
የጥናት ርዕሶች
▪ ፍጥረት ሕያው የሆነውን አምላክ ይገልጣል
የሚታየውን አጽናፈ ዓለም የፈጠረው የማይታይ አምላክ ነው። ይህ እውነት መሆኑን ከልብህ ታምናለህ? እንዲህ ዓይነት እምነት ያላቸው ሁሉም ሰዎች አይደሉም። ሰዎች ስለ ፈጣሪ እውነቱን እንዲገነዘቡ መርዳት እንዲሁም እኛ ራሳችን በእሱ ላይ ያለንን እምነት ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው? ይህ ጉዳይ በዚህ ርዕስ ላይ ይብራራል።
▪ “ይሖዋን እንደ ባሪያ አገልግሉ”
ክርስቲያኖች ይሖዋን እንደ ባሪያ እንዲያገለግሉ ተበረታትተዋል። ይህ ርዕስ፣ በሙሴ ሕግ ውስጥ ባሪያዎችን አስመልክቶ ስለተደረገው ዝግጅት፣ የሰይጣን እና በእሱ ቁጥጥር ሥር ያለው ዓለም ባሪያ ላለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲሁም አምላክን እንደ ባሪያ በታማኝነት ማገልገል ምን በረከቶች እንደሚያስገኝ ያብራራል።
▪ በሚገባ ከታሰበበት ጸሎት የምናገኘው ትምህርት
▪ ፍቅር ከተንጸባረቀበት የኢየሱስ ጸሎት ጋር ተስማምቶ መኖር
በአምላክ ቃል ላይ በየቀኑ የምናሰላስል ከሆነ የምናቀርበው ጸሎት ትርጉም ያለው ይሆናል። ሌዋውያን የአምላክን ሕዝቦች ወክለው ያቀረቡት ጸሎት ይህ እውነት መሆኑን የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ በመጀመሪያው ርዕስ ላይ ተብራርቷል። ሁለተኛው ርዕስ ደግሞ ፍቅር ከተንጸባረቀበት የኢየሱስ ጸሎት ጋር ተስማምተን መኖር የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያሳያል። ከሁለቱም ጸሎቶች እንደምንማረው ከግል ልመናችን በፊት ማስቀደም ያለብን ከይሖዋ ፈቃድ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ነው።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
ሽፋኑ፦ አንድ አስፋፊ፣ በአቲትላን ሐይቅ አጠገብ በምትገኝ ፓናጃቼል የተባለች ትንሽ ከተማ ሲሰብክ። በጓቲማላ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ከስፓንኛ በተጨማሪ በ11 የአገሪቱ ቋንቋዎች ምሥራቹን ይሰብካሉ
ጓቲማላ
የሕዝብ ብዛት፦
15,169,000
አስፋፊዎች፦
34,693
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፦
47,606