የርዕስ ማውጫ
ኅዳር 15, 2013
© 2013 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania.
የጥናት እትም
ታኅሣሥ 30, 2013–ጥር 5, 2014
ገጽ 3 • መዝሙሮች፦ 51, 54
ጥር 6-12, 2014
“በትዕግሥት የመጠበቅ ዝንባሌ” ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?
ገጽ 10 • መዝሙሮች፦ 20, 32
ጥር 13-19, 2014
በዛሬው ጊዜ ሰባቱ እረኞችና ስምንቱ አለቆች እነማን ናቸው?
ገጽ 16 • መዝሙሮች፦ 43, 42
ጥር 20-26, 2014
ገጽ 21 • መዝሙሮች፦ 43, 31
ጥር 27, 2014–የካቲት 2, 2014
እረኞች፣ ከሁሉ የላቁትን እረኞች አርዓያ ተከተሉ
ገጽ 26 • መዝሙሮች፦ 5, 25
የጥናት ርዕሶች
▪ “በጸሎት ረገድ ንቁዎች ሁኑ”
የሰይጣን ክፉ ሥርዓት ለመጥፋት በተቃረበበት በዚህ ጊዜ በመንፈሳዊ ንቁ መሆናችን በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ርዕስ በጸሎት ረገድ ንቁዎች መሆናችን በመንፈሳዊ እንዳናንቀላፋ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
▪ “በትዕግሥት የመጠበቅ ዝንባሌ” ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?
ይህ ርዕስ ነቢዩ ሚክያስ ካሳየው ትዕግሥት ምን ትምህርት እንደምናገኝ ያብራራል። ይሖዋ ይህን ክፉ ሥርዓት የሚያጠፋበት ጊዜ መቅረቡን የሚያመላክቱት ክስተቶች ምን እንደሆኑ እንመለከታለን። በተጨማሪም ለአምላክ ትዕግሥት ያለንን አድናቆት እንዴት ማሳየት እንደምንችል እንመረምራለን።
▪ በዛሬው ጊዜ ሰባቱ እረኞችና ስምንቱ አለቆች እነማን ናቸው?
በሕዝቅያስ ዘመን ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ለመሰንዘር ስላሰበው ጥቃት ከሚናገረው ዘገባ ጠቃሚ ትምህርቶች እናገኛለን። በዚህ ርዕስ ውስጥ ያለው ሐሳብ ጉባኤውን በእረኝነት እንዲጠብቁ ኃላፊነት ለተሰጣቸው ወንድሞች ልዩ ትርጉም አለው።
▪ የይሖዋን እረኞች ታዘዙ
▪ እረኞች፣ ከሁሉ የላቁትን እረኞች አርዓያ ተከተሉ
“የይሖዋን እረኞች ታዘዙ” የሚለው የጥናት ርዕስ ይሖዋና ኢየሱስ በዛሬው ጊዜ በምድር የሚገኙትን በጎቻቸውን እንዴት እንደሚጠብቁ የሚገልጽ ሲሆን በእነሱ ሥር ያሉት በጎች ለሚደረግላቸው እንክብካቤ ምን ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው ያብራራል። ሁለተኛው የጥናት ርዕስ ደግሞ የጉባኤ ሽማግሌዎች የመንጋው የበታች እረኞች ሆነው ሲያገለግሉ ሊኖራቸው የሚገባውን አመለካከት ይገልጻል።
ሽፋኑ፦ በቶኪዮ በሚገኝ ባቡር ጣቢያ አስፋፊዎች በመንገድ ላይ ሲመሠክሩ። ከ2.8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በየዕለቱ ለሥራ ወደ ቶኪዮ ይመጣሉ። ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው የስብከቱ ሥራ አማካኝነት ቤታቸው ሊገኙ ያልቻሉትን ሰዎች ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው
ጃፓን
የሕዝብ ብዛት፦
126,536,000
አማካይ የአስፋፊዎች ቁጥር፦
216,692
የዘወትር አቅኚዎች፦
65,245