የርዕስ ማውጫ
ሚያዝያ 15, 2014
© 2014 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ሰኔ 2-8, 2014
ገጽ 3 • መዝሙሮች፦ 33, 49
ሰኔ 9-15, 2014
ገጽ 8 • መዝሙሮች፦ 54, 46
ሰኔ 16-22, 2014
ገጽ 17 • መዝሙሮች፦ 31, 27
ሰኔ 23-29, 2014
ገጽ 22 • መዝሙሮች፦ 22, 1
ሰኔ 30, 2014–ሐምሌ 6, 2014
ይሖዋ የሚመለከተን ለእኛ ጥቅም እንደሆነ ይሰማሃል?
ገጽ 27 • መዝሙሮች፦ 11, 6
የጥናት ርዕሶች
▪ እምነት በማሳየት ረገድ ሙሴን ምሰሉ
▪ “የማይታየው” አምላክ ይታይሃል?
ሙሴ እምነት ስለነበረው በዓይኑ ከሚያየው ባሻገር ያለውን ነገር ማየት ችሏል። እነዚህ ርዕሶች እኛም ልክ እንደ ሙሴ እምነት ማሳየት ብሎም ‘የማይታየውን አምላክ እንደምናየው አድርገን በጽናት መቀጠል’ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራሉ።—ዕብ. 11:27
▪ ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚችል የለም
▪ ደፋር ሁን—ይሖዋ ረዳትህ ነው!
በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራ ፍለጋ ይሰደዳሉ። ብዙዎች የሚሰደዱት የትዳር ጓደኛቸውንና ልጆቻቸውን ጥለው ነው። እነዚህ ርዕሶች ይሖዋ ለቤተሰብ ኃላፊነት ስላለው አመለካከትና ይህን ግዴታችንን መወጣት እንድንችል እኛን ስለሚረዳበት መንገድ ይገልጻሉ።
▪ ይሖዋ የሚመለከተን ለእኛ ጥቅም እንደሆነ ይሰማሃል?
“የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው” የሚለውን ጥቅስ ስናነብ አንዳንዶቻችን አምላክ ይህን የሚያደርገው ሕዝቡ ሕጉን እንዲፈጽሙ ለማስገደድ እንደሆነ አድርገን እናስብ ይሆናል፤ ምናልባትም ይህ አመለካከት ለእሱ ጤናማ ያልሆነ ፍርሃት አሳድሮብን ሊሆን ይችላል። (ምሳሌ 15:3) ይሁንና ይህ ርዕስ ይሖዋ የሚከታተለን መሆኑ በአምስት መንገዶች ጥቅም እንዳለው ይገልጻል።
ሽፋኑ፦ በኢስታንቡል አንድ ወንድም ፀጉሩን ለሚያስተካክለው ሰው ምሥራች የተባለውን ብሮሹር በመስጠት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲመሠክር
ቱርክ
የሕዝብ ብዛት
75,627,384
አስፋፊዎች
2,312
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
1,632
ሬሾ
1 የይሖዋ ምሥክር ለ32,711 ሰዎች
ከ2004 ወዲህ በቱርክ የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር ጭማሪ 165%