የርዕስ ማውጫ
ነሐሴ 15, 2014
© 2014 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
መስከረም 29, 2014–ጥቅምት 5, 2014
ጥቅምት 6-12, 2014
ገጽ 11 • መዝሙሮች፦ 37, 10
ጥቅምት 13-19, 2014
ገጽ 16 • መዝሙሮች፦ 51, 48
ጥቅምት 20-26, 2014
ገጽ 21 • መዝሙሮች፦ 26, 11
የጥናት ርዕሶች
▪ ሴቶች በይሖዋ ዓላማ ውስጥ ምን ሚና አላቸው?
በኤደን ገነት ውስጥ በአምላክ ላይ የተነሳው ዓመፅ በወንዶችም ሆነ በሴቶች ላይ ምን ውጤት እንዳስከተለ እንመለከታለን። በተጨማሪም በጥንት ዘመን የኖሩ አምላክን የሚፈሩ አንዳንድ ሴቶች ያከናወኑትን ነገር እንዲሁም በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያን ሴቶች በአምላክ ዓላማ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንመረምራለን።
▪ የአምላክ ቃል ሕያው ነው—ተጠቀሙበት!
ሁሉም የመንግሥቱ አስፋፊዎች በአገልግሎታቸው ውጤታማ መሆን ይፈልጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስንና ትራክቶቻችንን ተጠቅመን ከሰዎች ጋር ውይይት መጀመርና ሕያው በሆነው የይሖዋ ቃል አማካኝነት ልባቸውን መንካት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ? እስቲ አንዳንድ ጠቃሚ ዘዴዎችን እንመልከት።
▪ ይሖዋ ወደ እኛ የሚቀርበው እንዴት ነው?
ከፈጣሪያችን ጋር የቀረበ ዝምድና መመሥረት ይኖርብናል። ይሖዋ ቤዛውን ማዘጋጀቱና መጽሐፍ ቅዱስን ማስጻፉ ወደ እሱ መቅረብ እንድንችል ቅድሚያውን እንደወሰደ የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ እንመርምር።
▪ የትም ብትሆን የይሖዋን ድምፅ ስማ
በእውነት መንገድ መጽናት ከፈለግን ይሖዋ የሚነግረንን ማዳመጥ አለብን። ሰይጣን እንዲሁም ያለብን የኃጢአት ዝንባሌ እንቅፋት ቢፈጥሩብንም የይሖዋን ድምፅ መስማት የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመልከት። ይህ ርዕስ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ ያለውን አስፈላጊነት እንድንገነዘብ ይረዳናል።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
31 ከታሪክ ማኅደራችን
ሽፋኑ፦ እህቶች በቴል አቪቭ ባሕር ዳርቻ ላይ በሩሲያኛ ሲሰብኩ። ከበስተ ጀርባ የጃፋ ዓለታማ ኮረብታዎች ይታያሉ፤ የጥንቷ የኢዮጴ ወደብ የሚገኘው እዚህ ነበር
እስራኤል
የሕዝብ ብዛት
8,050,000
በ2013 ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር
1,459
በ2013 በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ ሰዎች
2,671