የርዕስ ማውጫ
መስከረም 15, 2014
© 2014 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ከጥቅምት 27, 2014–ኅዳር 2, 2014
ገጽ 7 • መዝሙሮች፦ 28, 16
ከኅዳር 3-9, 2014
“ብዙ መከራ” ቢኖርም አምላክን በታማኝነት አገልግሉ
ገጽ 12 • መዝሙሮች፦ 24, 49
ከኅዳር 10-16, 2014
ገጽ 17 • መዝሙሮች፦ 41, 24
ከኅዳር 17-23, 2014
ገጽ 23 • መዝሙሮች፦ 12, 5
ከኅዳር 24-30, 2014
የጥናት ርዕሶች
▪ እውነትን እንዳገኘህ እርግጠኛ ነህ? ለምን?
ይህ ርዕስ፣ በርካታ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች እውነትን እንደያዙ እርግጠኛ እንዲሆኑ ያደረጓቸውን አንዳንድ ምክንያቶች ያብራራል። በተጨማሪም የይሖዋ ምሥክሮች ራሳቸው እውነትን እንዳገኙ እርግጠኛ የሆኑት ለምን እንደሆነ እንመረምራለን።
▪ “ብዙ መከራ” ቢኖርም አምላክን በታማኝነት አገልግሉ
በሰይጣን ዓለም ውስጥ እስከኖርን ድረስ መከራ የማይቀር ነገር ነው። የሚያጋጥሙን አንዳንድ መከራዎች በእምነታችን ላይ የሚሰነዘሩ ቀጥተኛ ጥቃቶች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ስውር ናቸው። ይህ ርዕስ እነዚህን ጥቃቶች ለይተን እንድናውቅና ሰይጣን ለሚሰነዝረው ጥቃት እንድንዘጋጅ ይረዳናል።
▪ ወላጆች—ልጆቻችሁን እንደ እረኛ ተንከባከቧቸው
ወላጆች ልጆቻቸውን “በይሖዋ ተግሣጽ እንዲሁም የእሱን አስተሳሰብ በውስጣቸው በመቅረጽ” እንዲያሳድጉ ተመክረዋል። (ኤፌ. 6:4) ይህ ርዕስ ወላጆች ይህን ማድረግ የሚችሉባቸውን ሦስት መንገዶችና ለልጆቻቸው መንፈሳዊ እረኛ መሆን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
▪ የመጨረሻው ጠላት ሞት ይደመሰሳል
በሰው ልጆች ላይ ሞት የመጣው እንዴት ነው? “የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት [የሚደመሰሰው]” እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 15:26) ለእነዚህ ጥያቄዎች የተሰጡት መልሶች የይሖዋን ፍትሕ፣ ጥበብና በተለይ ደግሞ ፍቅሩን ጎላ አድርገው የሚያሳዩት እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።
▪ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉትን አስቧቸው
ከጥንት ዘመን ጀምሮ ይሖዋ፣ የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም እሱን በሙሉ ጊዜ የሚያገለግሉ ታማኝ ሕዝቦች ነበሩት። የእነዚህን ክርስቲያኖች ‘የእምነት ሥራና ከፍቅር የመነጨ ድካም እንደምናስብ’ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?—1 ተሰ. 1:3
ሽፋኑ፦ ሁለት ወንድሞች በስሪ ላንካ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ በሚገኘው በኔጎምቦ ለአንድ ዓሣ አጥማጅ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ሲሰብኩ
ስሪ ላንካ
የሕዝብ ብዛት
20,860,000
አስፋፊዎች
5,600
የዘወትር አቅኚዎች
641