የርዕስ ማውጫ
ኅዳር 15, 2014
© 2014 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ከታኅሣሥ 29, 2014–ጥር 4, 2015
ከጥር 5-11, 2015
ገጽ 8 • መዝሙሮች፦ 20, 17
ከጥር 12-18, 2015
ገጽ 13 • መዝሙሮች፦ 32, 27
ከጥር 19-25, 2015
ገጽ 18 • መዝሙሮች፦ 46, 18
ከጥር 26, 2015–የካቲት 1, 2015
የጥናት ርዕሶች
▪ የኢየሱስ ትንሣኤ ለእኛ ምን ትርጉም አለው?
ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳና በአሁኑ ጊዜ ሕያው እንደሆነ እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው? በተጨማሪም ይህ ርዕስ ክርስቶስ ከሞት ተነስቶ በሰማይ የማይጠፋ ሕይወት ማግኘቱ በእኛም ሆነ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች በመሆን በምናከናውነው እንቅስቃሴ ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ያብራራል።
▪ ቅዱስ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?
▪ በምግባራችን ሁሉ ቅዱስ መሆን አለብን
በዋነኝነት በዘሌዋውያን መጽሐፍ ላይ የተመሠረቱት እነዚህ ርዕሶች ይሖዋ ሕዝቡ ቅዱስ እንዲሆን የሚፈልገው ለምን እንደሆነና ይህን ባሕርይ ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራሉ። በተጨማሪም በምግባራችን ሁሉ ቅዱስ መሆን የምንችልባቸው መንገዶች ተጠቅሰዋል።
▪ “አምላኩ ይሖዋ የሆነለት ሕዝብ”
▪ ‘አሁን የአምላክ ሕዝብ ናችሁ’
መጽሐፍ ቅዱስ የምናስጠናቸው አንዳንድ ሰዎች ይሖዋ በምድር ላይ አንድ ድርጅት ብቻ እንዳለው ማመን ይከብዳቸዋል። አንድ ሰው በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ቢሆን ቅን ልቦና እስካለው ድረስ አምላክ እንደሚቀበለው ይሰማቸዋል። እነዚህ ርዕሶች የይሖዋን ሕዝቦች ማወቅና ከእነሱ ጋር ሆኖ ይሖዋን ማገልገል አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራሉ።
ሽፋኑ፦ የመንግሥቱ አስፋፊዎች፣ በኩባ ውስጥ በሙዚቃና በባሕላዊ ውዝዋዜ በምትታወቀውና የአገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ በሆነችው በሳንቲያጎ ዴ ኩባ ሲሰብኩ
ኩባ
የሕዝብ ብዛት
11,163,934
አስፋፊዎች
96,206
የዘወትር አቅኚዎች
9,040