የርዕስ ማውጫ
ጥር 15, 2015
© 2015 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ከመጋቢት 2-8, 2015
ከመጋቢት 9-15, 2015
ከመጋቢት 16-22, 2015
ትዳራችሁ ጠንካራና አስደሳች እንዲሆን ጥረት አድርጉ
ገጽ 18 • መዝሙሮች፦ 36, 51
ከመጋቢት 23-29, 2015
ይሖዋ ትዳራችሁን እንዲያጠናክረውና እንዲጠብቀው ፍቀዱ
ገጽ 23 • መዝሙሮች፦ 36, 50
ከመጋቢት 30, 2015–ሚያዝያ 5, 2015
የጥናት ርዕሶች
▪ ለይሖዋ ምስጋና አቅርቡለት፤ ትባረካላችሁ
ባሉን በረከቶች ላይ ማሰላሰልና ለእነዚህ በረከቶች ይሖዋን ማመስገን፣ የአመስጋኝነት መንፈስ ለማዳበር ብሎም ምንጊዜም አመስጋኝ ለመሆን ይረዳናል። ይህ መንፈስ፣ አመስጋኝ ያለመሆን ዝንባሌን ለማስወገድና ከባድ ፈተናዎችን ለመቋቋም ያስችለናል። የ2015 የዓመት ጥቅሳችን ዓመቱን ሙሉ ይህንን እንድናስታውስ ይረዳናል።
▪ የጌታ ራትን የምናከብረው ለምንድን ነው?
ይህ ርዕስ የኢየሱስን ሞት የምናከብረው ለምን እንደሆነ ያብራራል። በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚቀርቡት ቂጣና የወይን ጠጅ ምን እንደሚያመለክቱ እንዲሁም አንድ ሰው ከቂጣውና ከወይን ጠጁ መካፈል ይገባው እንደሆነና እንዳልሆነ እንዴት ማወቅ እንደሚችል ይገልጻል። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ጥናት፣ በግለሰብ ደረጃ ለጌታ ራት መዘጋጀት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስገነዝበናል።
▪ ትዳራችሁ ጠንካራና አስደሳች እንዲሆን ጥረት አድርጉ
▪ ይሖዋ ትዳራችሁን እንዲያጠናክረውና እንዲጠብቀው ፍቀዱ
ባለትዳሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የሚሄዱ ተጽዕኖዎችና ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል። ያም ቢሆን በይሖዋ እርዳታ ትዳራቸው ጠንካራና አስደሳች እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ። በመጀመሪያው የጥናት ርዕስ ላይ፣ ቤት ለመገንባት እንደሚያገለግለው ጡብ ትዳርን ጠንካራና ዘላቂ ለማድረግ የሚረዱ አምስት ነገሮችን እንዲሁም ጡቦቹ በምን እንደሚያያዙ እንመለከታለን። በሁለተኛው የጥናት ርዕስ ላይ ደግሞ ባልና ሚስት የሥነ ምግባር አቋማቸውን መጠበቅ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ እናያለን።
▪ የማይከስም ፍቅር ሊኖር ይችላል?
በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚኖረው እውነተኛ ፍቅር ምን ይመስላል? የማይከስም ፍቅር ሊኖር ይችላል? እንዲህ ያለው ፍቅር የሚገለጸው እንዴት ነው? የማይከስም ፍቅርን በተመለከተ ከማሕልየ መሓልይ መጽሐፍ ምን መማር እንደምንችል እንመለከታለን።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
ሽፋኑ፦ ውብ በሆነችው በግሪንድልዋልድ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሞ መመሥከር፤ በአልፕስ የተራራ ሠንሠለት ላይ የሚገኘው በርኒዝ ከበስተ ጀርባ ይታያል
ስዊዘርላንድ
የሕዝብ ብዛት
7,876,000
አስፋፊዎች
18,646
በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ (2013)
31,980