የርዕስ ማውጫ
የግንቦት 15, 2015
© 2015 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ከሰኔ 29, 2015–ሐምሌ 5, 2015
ገጽ 9 • መዝሙሮች፦ 54, 43
ከሐምሌ 6-12, 2015
ከሰይጣን ጋር ተዋግታችሁ ልታሸንፉት ትችላላችሁ!
ገጽ 14 • መዝሙሮች፦ 60, 100
ከሐምሌ 13-19, 2015
ገጽ 19 • መዝሙሮች፦ 81, 134
ከሐምሌ 20-26, 2015
ገጽ 24 • መዝሙሮች፦ 12, 69
የጥናት ርዕሶች
▪ ንቁ ሆናችሁ ኑሩ—ሰይጣን ሊውጣችሁ ይፈልጋል!
▪ ከሰይጣን ጋር ተዋግታችሁ ልታሸንፉት ትችላላችሁ!!
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰይጣንን ከሚያገሳ አንበሳ ጋር ያመሳስለዋል። ሰይጣን ኃያል፣ አረመኔና አታላይ ነው። እነዚህ የጥናት ርዕሶች፣ ይህን አደገኛ ጠላት በጽናት መቃወም ያለብን ለምን እንደሆነ ያብራራሉ። በተጨማሪም በሰይጣን የማታለያ ዘዴዎች እንዳንሸነፍ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንደምንችል ይጠቁሙናል።
▪ ተስፋ የተሰጠበትን ነገር ‘አዩት’
▪ የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሰጠንን አምላክ ምሰሉ
ፈጽሞ አይተናቸው ወይም አጋጥመውን የማያውቁ ነገሮችን በዓይነ ሕሊናችን የመሳል ችሎታችንን፣ ጥበብ በሚንጸባረቅበት አሊያም ጎጂ በሆነ መንገድ ልንጠቀምበት እንችላለን። በእነዚህ ርዕሶች ውስጥ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮችን እንመለከታለን። ያላየናቸውን ነገሮች በአእምሯችን የመሳል ችሎታችን እምነት ለማዳበር የሚረዳን እንዲሁም ይሖዋን በፍቅሩ፣ በደግነቱ፣ በጥበቡና ደስተኛ በመሆኑ ለመምሰል የሚያስችለን እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።
ሽፋኑ፦ ሁለት ወንድሞች አንድን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስጠኑ
አርሜንያ
የሕዝብ ብዛት
3,026,900
አስፋፊዎች
11,143
የዘወትር አቅኚዎች
2,205
23,844
ሚያዝያ 14, 2014 በተከበረው የመታሰቢያ በዓል ላይ የተገኙ ሰዎች ቁጥር ከአስፋፊዎቹ በእጥፍ ይበልጣል