የርዕስ ማውጫ
መስከረም 15, 2015
© 2015 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት ርዕሶች
ከጥቅምት 26, 2015–ኅዳር 1, 2015
ክርስቶስ የደረሰበት የጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ እየተጣጣራችሁ ነው?
ገጽ 3
ከኅዳር 2-8, 2015
ገጽ 8
ከኅዳር 9-15, 2015
ገጽ 13
ከኅዳር 16-22, 2015
ገጽ 18
ከኅዳር 23-29, 2015
ይሖዋን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ገጽ 23
የጥናት ርዕሶች
▪ ክርስቶስ የደረሰበት የጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ እየተጣጣራችሁ ነው?
▪ ሕሊናችሁ አስተማማኝ መሪ ነው?
የአምላክ አገልጋዮች በመንፈሳዊ የጎለመሱ ለመሆን መንፈሳዊ እድገት ማድረግ እንዳለባቸው ይገነዘባሉ። በተጨማሪም አምላክ የሰጣቸውን ሕሊና ማሠልጠን ይኖርባቸዋል። እነዚህ የጥናት ርዕሶች ጉልምስና እና ሕሊና በተለያዩ የሕይወታችን ዘርፎች የሚጫወቱትን ሚና በማብራራት ግሩም መመሪያ ይሰጣሉ።
▪ “በእምነት ጸንታችሁ ቁሙ”
ጴጥሮስ በገሊላ ባሕር ላይ ለመራመድ ካደረገው ሙከራ ስለ እምነት ግሩም ትምህርት እናገኛለን። ይህ ርዕስ እምነታችን የተዳከመበትን አቅጣጫ ለይተን ማወቅ የምንችልበትን መንገድ የሚጠቁም ከመሆኑም ሌላ እምነታችንን ማጠናከር የምንችልበትን መንገድ ያብራራል።
▪ ይሖዋ ፍቅሩን ያሳየን በየትኞቹ መንገዶች ነው?
▪ ይሖዋን እንደምንወደው ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ እንደሚወደን ማወቃችንና እኛም በአጸፋው እሱን መውደዳችን በሕይወታችን ውስጥ ይህ ነው የማይባል እርካታና ደስታ ይሰጠናል። በእነዚህ ሁለት ርዕሶች ውስጥ ይሖዋ ለእኛ ፍቅሩን ያሳየባቸውን መንገዶችና እኛም በአጸፋው ለእሱ ፍቅራችንን ማሳየት የምንችልባቸውን መንገዶች እንመለከታለን።
በተጨማሪም በዚህ እትም ውስጥ
ሽፋኑ፦ በቻይንኛ ጉባኤ የሚያገለግሉ ጣሊያናውያን አስፋፊዎች የሮምን ከተማ ለሚጎበኙ ቱሪስቶች ሲመሠክሩ። በአንድ ጥንታዊ ሕንፃ አጠገብ ያለው ተንቀሳቃሽ የጽሑፍ መደርደሪያችን በየወሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ትኩረት ይስባል
ጣሊያን
የሕዝብ ብዛት
60,782,668
አስፋፊዎች
251,650
አቅኚዎች
33,073
ከ24,000 በላይ የሚሆኑ አስፋፊዎች ምሥራቹን በ37 የውጭ አገር ቋንቋዎች እየሰበኩ ናቸው