የርዕስ ማውጫ
ኅዳር 15, 2015
© 2015 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
የጥናት እትም
ከታኅሣሥ 28, 2015–ጥር 3, 2016
ልጃችሁ ይሖዋን እንዲያገለግል አሠልጥኑት—ክፍል 1
ገጽ 3
ከጥር 4-10, 2016
ልጃችሁ ይሖዋን እንዲያገለግል አሠልጥኑት—ክፍል 2
ገጽ 8
ከጥር 11-17, 2016
ገጽ 16
ከጥር 18-24, 2016
ገጽ 21
ከጥር 25-31, 2016
ገጽ 26
የጥናት ርዕሶች
▪ ልጃችሁ ይሖዋን እንዲያገለግል አሠልጥኑት—ክፍል 1
▪ ልጃችሁ ይሖዋን እንዲያገለግል አሠልጥኑት—ክፍል 2
ይሖዋ ለወላጆች አስደሳች ሆኖም በቁም ነገር ሊያዩት የሚገባ ኃላፊነት ሰጥቷቸዋል፤ ይህ ኃላፊነት፣ ልጆቻቸው አምላክን እንዲያገለግሉ ማሠልጠን ነው። እነዚህ ሁለት ርዕሶች ወላጆች፣ ኢየሱስን በመምሰል እንዲሁም እሱ ያሳያቸውን ሦስት ባሕርያት ይኸውም ፍቅርን፣ ትሕትናንና ማስተዋልን በማንጸባረቅ ኃላፊነታቸውን እንዴት መወጣት እንደሚችሉ ያብራራል።
▪ ይሖዋ የፍቅር አምላክ ነው
▪ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ትወዳለህ?’
የመጀመሪያው ርዕስ ይሖዋ የፍቅር አምላክ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። በተጨማሪም አምላክ ለሰው ዘር ያለውን ፍቅር ያሳየበትን መንገድ ያብራራል። በሁለተኛው ርዕስ ላይ ደግሞ የይሖዋ አገልጋዮች ለባልንጀራቸው እንዴት ፍቅር እንደሚያሳዩ እንመረምራለን።
▪ በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር ያሳለፍነው መቶ ዓመት!
ይህ ርዕስ የአምላክ መንግሥት ሲገዛ በቆየባቸው ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ ምሥራቹን ከማወጅ ጋር በተያያዘ ምን እንደተከናወነ ይገልጻል። ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ላይ ስለተጠቀምንባቸው አንዳንድ መሣሪያዎችና አዳዲስ ዘዴዎች አንብብ። በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት የመንግሥቱ አስፋፊዎች ያገኟቸውን ውጤታማ ሥልጠናዎች መርምር።
ሽፋኑ፦ አንድ የወረዳ የበላይ ተመልካችና የተወሰኑ ልዩ አቅኚዎች በአማዞን አካባቢ በጀልባ ሲጓዙ። በአማዞን ወንዝና ገባር በሆኑት ወንዞች ዳርቻ ላይ ባሉ ርቀው የሚገኙ መንደሮች ምሥራቹን በደስታ ያውጃሉ
ብራዚል
የሕዝብ ብዛት
203,067,835
አስፋፊዎች
794,766
አቅኚዎች
84,550
በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ (2014)