የርዕስ ማውጫ
ከግንቦት 30, 2016–ሰኔ 5, 2016 ባለው ሳምንት
5 በይሖዋ ላይ እምነት ማሳደር የእሱን ሞገስ ያስገኛል
ይህ ርዕስ ዮፍታሔና ሴት ልጁ፣ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም የአምላክን መመሪያዎች እንዲከተሉ የረዳቸው ምን እንደሆነ ያብራራል። በተጨማሪም የአምላክን ሞገስ ማግኘት፣ ማንኛውም መሥዋዕትነት ሊከፈልለት የሚገባ ነገር ነው የምንለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።
10 በዓይነ ሕሊና የማየት ችሎታህን በጥበብ እየተጠቀምክበት ነው?
ከሰኔ 6-12, 2016 ባለው ሳምንት
የዘላለም ሕይወት ለማግኘት እስከ መጨረሻው መጽናት ይኖርብናል። ይህ ርዕስ ለመጽናት የሚረዱንን አራት ነጥቦች ያብራራል፤ በተጨማሪም በጽናት ረገድ ልንመስላቸው የሚገቡ ሦስት ምሳሌዎችን እንመለከታለን። ጽናት በእያንዳንዳችን ላይ ስለሚፈጽመው ሥራም ይብራራል።
ከሰኔ 13-19, 2016 ባለው ሳምንት
18 ለአምልኮ አንድ ላይ መሰብሰብ ያለብን ለምንድን ነው?
ሁሉም ክርስቲያኖች፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ከባድ እንዲሆንባቸው የሚያደርጉ እንቅፋቶች ያጋጥሟቸዋል። ይህ ርዕስ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘታችን እኛንና ሌሎችን የሚጠቅመው እንዲሁም ይሖዋ አምላክን የሚያስደስተው እንዴት እንደሆነ ያብራራል፤ ይህን ማወቃችን የሚያጋጥሙንን እንቅፋቶች መወጣት እንድንችል ብርታት ይሰጠናል።
23 የሕይወት ታሪክ—የቀድሞዎቹ መነኮሳት እውነተኛ መንፈሳዊ እህትማማቾች ሆኑ
ከሰኔ 20-26, 2016 ባለው ሳምንት
27 በተከፋፈለ ዓለም ውስጥ የገለልተኝነት አቋማችሁን ጠብቁ
ሰብዓዊ መንግሥታት መጨረሻቸው እየቀረበ ሲመጣ፣ የገለልተኝነት አቋማችን ይበልጥ እያስቆጣቸው እንደሚሄድ እንጠብቃለን። ይህ ርዕስ የገለልተኝነት አቋማችንን እንድንጠብቅና አቋማችንን እንዳናላላ የሚረዱንን አራት ነጥቦች ያብራራል።