የርዕስ ማውጫ
ከጥቅምት 23-29, 2017 ባለው ሳምንት
ይሖዋ ራስን በመግዛት ረገድ ከሁሉ የላቀ ምሳሌ ትቶልናል። የሰው ልጆች ይሖዋን በመምሰል ራስን የመግዛት ባሕርይን ማንጸባረቅ የሚችሉት እንዴት ነው? ራስህን ለመግዛት ምን እርምጃዎችን መውሰድ ትችላለህ?
ከጥቅምት 30, 2017–ኅዳር 5, 2017 ባለው ሳምንት
ሩኅሩኅ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው? ይሖዋና ኢየሱስ ይህን ባሕርይ በማንጸባረቅ ረገድ ፍጹም የሆነ ምሳሌ ትተውልናል። የእነሱን ምሳሌ በመከተል ርኅራኄ ማሳየት የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው? እንዲህ ማድረጋችንስ ምን ጥቅም ያስገኝልናል?
13 የሕይወት ታሪክ—መንፈሳዊ ከሆኑ ሰዎች ጋር በመሥራቴ ተባርኬያለሁ
ከኅዳር 6-12, 2017 ባለው ሳምንት
18 “የአምላካችን ቃል . . . ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል”
ከኅዳር 13-19, 2017 ባለው ሳምንት
መጽሐፍ ቅዱስ በበርካታ ቋንቋዎች የሚገኝ መሆኑና ይህ መጽሐፍ የሚገኝባቸው ቋንቋዎች ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመሩ መሆናቸው ትኩረታችንን የሚስበው ለምንድን ነው? የአምላክን ቃል በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ስላገኘን አመስጋኞች መሆናችንን ማሳየት የምንችለውስ እንዴት ነው? እነዚህ ርዕሶች ለመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ይህን መጽሐፍ ለሰጠን አካል ያለንን አድናቆት ለማሳደግ ይረዱናል።
ከኅዳር 20-26, 2017 ባለው ሳምንት
ክርስቲያኖች ደፋር መሆን ያስፈልጋቸዋል። ድፍረት በማሳየት ረገድ ምሳሌ ከሚሆኑ በጥንት ዘመን የኖሩ ሰዎች ምን እንማራለን? ወጣቶች፣ ወላጆች፣ በዕድሜ የገፉ እህቶችና የተጠመቁ ወንድሞች ድፍረት እንዳላቸውና ይሖዋ የሰጣቸውን ሥራ ለማከናወን ዝግጁ እንደሆኑ ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?