የርዕስ ማውጫ
ከየካቲት 26, 2018–መጋቢት 4, 2018 ባለው ሳምንት
በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ችግሮች ከአቅማችን በላይ እንደሆኑ ሲሰማን ምን እናደርጋለን? ይህ ርዕስ የ2018ን የዓመት ጥቅስ ያብራራል፤ በተጨማሪም ይሖዋ እኛን ለማበርታት ባደረጋቸው ዝግጅቶች መጠቀም ያለብን ለምን እንደሆነና ይሖዋ እንዴት እንደሚያበረታን ይገልጻል።
ከመጋቢት 5-11, 2018 ባለው ሳምንት
12 የመታሰቢያው በዓል ለአንድነታችን አስተዋጽኦ የሚያደርገው እንዴት ነው?
በዚህ ዓመት የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል የሚውለው ቅዳሜ፣ መጋቢት 31, 2018 ነው። ለዚህ በዓል ከአሁኑ ዝግጅት ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? በበዓሉ ላይ መገኘታችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል? በየዓመቱ የሚከበረው ይህ በዓል ለአምላክ ሕዝቦች አንድነት አስተዋጽኦ የሚያደርገውስ እንዴት ነው? ይህ ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
ከመጋቢት 12-18, 2018 ባለው ሳምንት
17 የሁሉም ነገር ባለቤት ለሆነው አምላክ ምን ልንሰጠው እንችላለን?
ያለን ነገር ሁሉ ከይሖዋ ያገኘነው ነው። ያም ሆኖ ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ድርጅቱ ለሚያከናውነው ሥራ የገንዘብ ድጋፍ እንድናደርግ ይጠብቅብናል። ይህ ርዕስ፣ ባሉን ነገሮች ይሖዋን ማክበር ያለብን ለምንና እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
ከመጋቢት 19-25, 2018 ባለው ሳምንት
22 እውነተኛ ደስታ የሚያስገኘው ምን ዓይነት ፍቅር ነው?
ከመጋቢት 26, 2018–ሚያዝያ 1, 2018 ባለው ሳምንት
27 አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
የመጀመሪያው የጥናት ርዕስ፣ እውነተኛ ደስታ ማግኘት የምንችለው ይሖዋን በመውደድ እንጂ “በመጨረሻዎቹ ቀናት” የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ለሚወዷቸው ነገሮች ፍቅር በማዳበር እንዳልሆነ ያብራራል። (2 ጢሞ. 3:1) በሁለተኛው ርዕስ ላይ ደግሞ በመጨረሻው ዘመን በሚኖሩ ሰዎች ባሕርያትና የአምላክ ሕዝቦች በሚያሳዩአቸው ባሕርያት መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት እንመረምራለን።
32 ይህን ያውቁ ኖሯል?