የርዕስ ማውጫ
ከነሐሴ 6-12, 2018 ባለው ሳምንት
ከነሐሴ 13-19, 2018 ባለው ሳምንት
8 ይሖዋና ኢየሱስ አንድ እንደሆኑ ሁላችንም አንድ እንሁን
በኢየሱስ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ እንዲሁም የዘር ክፍፍል ነበር። ክርስቶስ፣ ተከታዮቹን አንድነት እንዲኖራቸውና መከፋፈል የሚፈጥረውን ጭፍን ጥላቻ እንዲያስወግዱ ያስተማራቸው እንዴት እንደሆነ በእነዚህ ሁለት ርዕሶች ላይ እንመለከታለን። በተጨማሪም የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የተዉት ምሳሌ፣ እኛም በዚህ የተከፋፈለ ዓለም ውስጥ አንድነታችንን ጠብቀን እንድንኖር እንዴት እንደሚረዳን እንመረምራለን።
ከነሐሴ 20-26, 2018 ባለው ሳምንት
16 የአምላክን ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች በመጠቀም ሕሊናችሁን አሠልጥኑ
ሕሊናችን በትክክለኛው አቅጣጫ እንዲመራን መሠልጠን አለበት። ይሖዋ ስለሚወደን ሕሊናችንን በሚገባ ለመቅረጽና የእሱ ዓይነት አመለካከት ለማዳበር የሚረዱንን ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ሰጥቶናል። ይህ ርዕስ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዴት በሥራ ላይ ማዋል እንደምንችል ይገልጻል።
ከነሐሴ 27, 2018–መስከረም 2, 2018 ባለው ሳምንት
ኢየሱስ፣ ብርሃናቸውን በማብራት አምላክን እንዲያስከብሩ ደቀ መዛሙርቱን አሳስቧቸዋል። በዚህ ርዕስ ውስጥ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ ማድረጋችን ‘ብርሃናችንን ይበልጥ ለማብራት’ ይረዳናል።
26 የሕይወት ታሪክ—በጭንቀቶቼ ሁሉ ማጽናኛ አግኝቻለሁ
30 ሰላምታ ያለው ኃይል
32 ታስታውሳለህ?