የርዕስ ማውጫ
ከመስከረም 3-9, 2018 ባለው ሳምንት
7 እውቅና ማግኘት የምትፈልጉት በማን ዘንድ ነው?
በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ሰዎች ይህ ክፉ ዓለም የሚሰጠውን እውቅና ለማግኘት ይጣጣራሉ። ይህ ርዕስ ከሁሉ የላቀውን እውቅና ማለትም ይሖዋ ለታማኝ አገልጋዮቹ የሚሰጠውን እውቅና በማግኘት ላይ ማተኮር ያለብን ለምን እንደሆነ ያብራራል። በተጨማሪም ይሖዋ አንዳንድ ጊዜ ፈጽሞ ባልተጠበቀ መንገድ እውቅና የሚሰጠው እንዴት እንደሆነ ያሳያል።
ከመስከረም 10-16, 2018 ባለው ሳምንት
በዚህ ርዕስ ውስጥ፣ ታማኝ የነበረው ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመግባት መብቱን ያጣው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን። በተጨማሪም ሙሴ በወደቀበት ወጥመድ ላለመውደቅ ምን ማድረግ እንዳለብን እንመረምራለን።
ከመስከረም 17-23, 2018 ባለው ሳምንት
ከመስከረም 24-30, 2018 ባለው ሳምንት
22 የይሖዋ ንብረት ነን
የሰው ዘር በሙሉ የይሖዋ ንብረት ነው። በመሆኑም ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የመጠየቅ መብት አለው። አንዳንዶች ግን በአንድ በኩል ለአምላክ ታማኝ መስለው እየታዩ በሌላ በኩል ደግሞ ዓመፀኝነት የሚንጸባረቅበት አካሄድ ይከተላሉ። በመጀመሪያው ርዕስ ላይ ስለ ቃየን፣ ስለ ሰለሞን፣ ስለ አሮንና ስለ ሙሴ ከሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ምን ጠቃሚ ትምህርት እንደምናገኝ እንመለከታለን። በሁለተኛው ርዕስ ላይ ደግሞ የይሖዋ ሕዝብ በመሆን ላገኘነው ውድ መብት አመስጋኝነታችንን ማሳየት የምንችልባቸውን የተለያዩ መንገዶች እንመረምራለን።