የርዕስ ማውጫ
ከታኅሣሥ 31, 2018–ጥር 6, 2019 ባለው ሳምንት
ከጥር 7-13, 2019 ባለው ሳምንት
እነዚህ ሁለት ርዕሶች ከይሖዋ የተማርናቸውን ውድ እውነቶች ምንጊዜም ከፍ አድርገን እንድንመለከት ያበረታቱናል። እነዚህን እውነቶች ለማግኘት ስንል የከፈልነው መሥዋዕት ካገኘነው በረከት ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በተጨማሪም እነዚህ ርዕሶች እውነትን ከፍ አድርገን መመልከታችንን ለመቀጠል እንዲሁም ለእውነት ስንል ከከፈልነው ዋጋ ላይ የተወሰነውን እንኳ መልሰን ላለመውሰድ ምን ማድረግ እንዳለብን ያብራራሉ።
ከጥር 14-20, 2019 ባለው ሳምንት
የዕንባቆም መጽሐፍ አስጨናቂ ሁኔታ ቢያጋጥመንም በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት ይዘን መቀጠል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል። ይህ ርዕስ፣ ያለብን ጭንቀት እንዲሁም የሚደርስብን መከራና ሥቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢሄድም በይሖዋ መታመናችን የኋላ ኋላ መዳን የሚያስገኝልን እንዴት እንደሆነ ያስገነዝበናል።
ከጥር 21-27, 2019 ባለው ሳምንት
ከጥር 28, 2019–የካቲት 3, 2019 ባለው ሳምንት
23 የይሖዋ ዓይነት አስተሳሰብ ለማዳበር ጥረት እያደረጋችሁ ነው?
በመንፈሳዊ እያደግን ስንሄድ የይሖዋ አስተሳሰብ የላቀ መሆኑን እንገነዘባለን። እነዚህ ሁለት ርዕሶች በዓለም አስተሳሰብ ላለመቀረጽና አስተሳሰባችንን ከይሖዋ አስተሳሰብ ጋር ለማስማማት ምን ማድረግ እንዳለብን ያብራራሉ።