የርዕስ ማውጫ
ከየካቲት 4-10, 2019 ባለው ሳምንት
እውነተኛ ክርስቲያኖች በገነት ውስጥ ለመኖር በጉጉት ይጠባበቃሉ። ይህ ርዕስ በገነት ውስጥ የመኖር ተስፋ እንዳለን የሚያሳዩ ጠንካራ ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎችን ይዟል፤ በተጨማሪም ኢየሱስ ገነትን አስመልክቶ የሰጠውን ተስፋ መረዳት የሚገባን እንዴት እንደሆነ ያብራራል።
9 ታስታውሳለህ?
ከየካቲት 11-17, 2019 ባለው ሳምንት
10 አምላክ ላቋቋመው የጋብቻ ዝግጅት አክብሮት ይኑራችሁ
ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ክቡር የሆነውን የጋብቻ ዝግጅት አስመልክቶ ምን እንደሚል ያብራራል። ለጋብቻ ዝግጅት አክብሮት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ፍቺንና መለያየትን አስመልክቶ የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?
15 የሕይወት ታሪክ—‘ይሖዋ ደግነት አሳይቶናል’
ከየካቲት 18-24, 2019 ባለው ሳምንት
19 ወጣቶች፣ ፈጣሪያችሁ ደስተኛ እንድትሆኑ ይፈልጋል
ከየካቲት 25, 2019–መጋቢት 3, 2019 ባለው ሳምንት
24 ወጣቶች፣ እርካታ ያለው ሕይወት መምራት ትችላላችሁ
አብዛኛውን ጊዜ ወጣቶች በሕይወታቸው ውስጥ ከባድ ውሳኔዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ለምሳሌ ከሚከታተሏቸው ግቦች ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ግልጽ ነው። በርካታ ሰዎች ከፍተኛ ትምህርት እንዲከታተሉና ዳጎስ ያለ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ እንዲይዙ ሊያበረታቷቸው ይችላሉ። ይሖዋ ግን በሕይወታቸው ውስጥ እሱን እንዲያስቀድሙ ይፈልጋል። እነዚህ ሁለት ርዕሶች አምላክን መስማት የጥበብ አካሄድ ነው የምንልበትን ምክንያት ያብራራሉ።