የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp19 ቁጥር 1 ገጽ 4-5
  • የአምላክ ስም ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ ስም ማን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክን ስም ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • የአምላክ ስም የሚገልጻቸው ነገሮች
  • የአምላክ ስም
    ንቁ!—2017
  • የአምላክን ስም ማወቅ የሚኖርብን ለምንድን ነው?
    ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም
  • በአምላክ ስም መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የይሖዋን ታላቅ ስም አክብሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
wp19 ቁጥር 1 ገጽ 4-5

የአምላክ ስም ማን ነው?

ከአንድ ሰው ጋር ስትተዋወቅ መጀመሪያ የምታቀርበው ጥያቄ “ስምህ ማን ነው?” የሚል ነው። ይህንኑ ጥያቄ አምላክን ብትጠይቀው ምን መልስ የሚሰጥህ ይመስልሃል?

“እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው።”—ኢሳይያስ 42:8

ይህን ስም ከዚህ በፊት ሰምተኸው አታውቅም? ሰምተኸው አታውቅ ይሆናል። ምክንያቱም በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች የአምላክን ስም አይጠቀሙም፤ ቢጠቀሙ እንኳ ከስንት አንዴ ነው። ብዙውን ጊዜ ስሙን “ጌታ” ወይም “እግዚአብሔር” እንደሚሉት ባሉ የማዕረግ ስሞች ይተኩታል። መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ ግን በአራቱ የዕብራይስጥ ፊደላት (በአማርኛ የሐወሐ) የሚወከለው የአምላክ ስም 7,000 ጊዜ ያህል ተጠቅሶ ይገኛል። በአማርኛ የተለመደው የዚህ ስም አጠራር “ይሖዋ” ነው።

የአምላክ ስም በዕብራይስጥ የተጻፈበት የሙት ባሕር ጥቅልል

የሙት ባሕር የመዝሙር መጽሐፍ ጥቅልል አንደኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. ዕብራይስጥ

የአምላክ ስም በእንግሊዝኛ የተጻፈበት የቲንደል ትርጉም

የቲንደል ትርጉም 1530፣ እንግሊዝኛ

የአምላክ ስም በስፓንኛ የተጻፈበት ሬና ቫሌራ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ

ሬና ቫሌራ ቨርዥን 1602፣ ስፓንኛ

የአምላክ ስም በቻይንኛ የተጻፈበት ዩኒየን ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ

ዩኒየን ቨርዥን 1919፣ ቻይንኛ

የአምላክ ስም በዕብራይስጡ ጽሑፍና በሌሎች በርካታ ትርጉሞች ውስጥ ይገኛል

የአምላክን ስም ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

አምላክ ራሱ ለስሙ ትልቅ ቦታ ይሰጣል። ይህ ስም ሌላ አካል ለአምላክ ያወጣለት ሳይሆን አምላክ ለራሱ የመረጠው ስም ነው። ይሖዋ “ይህ ለዘላለም ስሜ ነው፤ ከትውልድ እስከ ትውልድ የምታወሰውም በዚህ ነው” ብሎ ተናግሯል። (ዘፀአት 3:15) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአምላክ ስም ሁሉን ቻይ፣ አብ፣ ጌታ ወይም አምላክ እንደሚሉት ካሉ የማዕረግ ስሞች ሁሉ ይበልጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል። በተጨማሪም አብርሃም፣ ሙሴ፣ ዳዊት ወይም ኢየሱስ እንደሚሉት ካሉ የግል መጠሪያ ስሞች ይበልጥ በብዛት ተጠቅሷል። ከዚህም በላይ ይሖዋ ስሙ እንዲታወቅ ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ “ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ ሰዎች ይወቁ” ይላል።—መዝሙር 83:18

ኢየሱስ ለአምላክ ስም ትልቅ ቦታ ይሰጣል። አባታችን ሆይ ወይም አቡነ ዘበሰማያት ተብሎ በሚጠራው ጸሎት ላይ ኢየሱስ ተከታዮቹን “ስምህ ይቀደስ” ብለው ወደ አምላክ እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል። (ማቴዎስ 6:9) እሱ ራሱም “አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው” በማለት ጸልዮአል። (ዮሐንስ 12:28) ኢየሱስ በሕይወቱ ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ የሰጠው የአምላክን ስም ለማስከበር ነበር፤ በመሆኑም “ስምህን አሳውቄአቸዋለሁ፤ ደግሞም አሳውቃለሁ” ብሎ ሊጸልይ ችሏል።—ዮሐንስ 17:26

አምላክን የሚያውቁ ሰዎች ለስሙ ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ። በጥንት ዘመን የኖሩ የአምላክ ሕዝቦች የአምላክ ስም ጥበቃና መዳን እንደሚያስገኝላቸው ተገንዝበው ነበር። “የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው። ጻድቅ ወደዚያ በመሮጥ ጥበቃ ያገኛል።” (ምሳሌ 18:10) “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።” (ኢዩኤል 2:32) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ይህ ስም የአምላክን አገልጋዮች ለይቶ እንደሚያሳውቃቸው ይገልጻል። እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው በአምላካቸው ስም ይሄዳሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን።”—ሚክያስ 4:5፤ የሐዋርያት ሥራ 15:14

የአምላክ ስም የሚገልጻቸው ነገሮች

ስሙ የአምላክን ማንነት በሚገባ ይገልጻል። ብዙ ምሁራን ይሖዋ የሚለው ስም “እንዲሆን ያደርጋል” የሚል ትርጉም እንዳለው ያምናሉ። ይሖዋ አምላክ “መሆን የምፈልገውን እሆናለሁ” በማለት ለሙሴ የተናገረው ሐሳብ የስሙን ትርጉም ማስተዋል እንድንችል ይረዳናል። (ዘፀአት 3:14) ይህ ጥቅስ እንደሚያሳየው የአምላክ ስም ትርጉም እሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ በመሆን የተጫወተውን ሚና ብቻ የሚያመለክት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ዓላማውን ለማሳካት እሱ ራሱም ሆነ ፍጥረታቱ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲሆኑ የማድረግ ችሎታ እንዳለውም ያመለክታል። የአምላክ የማዕረግ ስሞች እሱ ያለውን ሥልጣን፣ ቦታ ወይም ኃይል የሚገልጹ ቢሆኑም ማንነቱንና የፈለገውን የመሆን ችሎታውን የሚገልጸው ይሖዋ የሚለው ስሙ ብቻ ነው።

ስሙ አምላክ ለእኛ ትኩረት እንደሚሰጠን ያሳያል። የአምላክ ስም ትርጉም አምላክ እኛን ጨምሮ ለሁሉም ፍጥረታቱ ምንጊዜም እንደሚያስብ ይጠቁማል። ከዚህም በላይ አምላክ ለእኛ ስሙን መንገሩ እሱን እንድናውቀው እንደሚፈልግ ያሳያል። ደግሞም ስሙን የነገረን እኛ ስለጠየቅነው ሳይሆን በራሱ ተነሳስቶ ነው። በግልጽ ማየት እንደሚቻለው አምላክ እሱን እንድንመለከተው የሚፈልገው ከእኛ በጣም እንደራቀና ማንነቱ እንደማይታወቅ መንፈስ አድርገን ሳይሆን እውን እንደሆነና ልንቀርበው እንደምንችል አካል አድርገን ነው።—መዝሙር 73:28

ስሙን መጠቀማችን ከእሱ ጋር መቀራረብ እንደምንፈልግ ያሳያል። በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ ልትቀርበው ለምትፈልገው አንድ ሰው ስምህን በተደጋጋሚ ነገርከው እንበል። ሆኖም ይህ ሰው በስምህ ሊጠራህ አይፈልግም። ታዲያ ይህ ሰው ከአንተ ጋር የመቀራረብ ፍላጎት እንዳለው ይሰማሃል? በጭራሽ! ከአምላክ ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ይሖዋ ለሰው ልጆች ስሙን ያሳወቃቸው ከመሆኑም ሌላ በዚህ ስም እንዲጠቀሙ ይፈልጋል። በይሖዋ ስም መጠቀማችን ወደ እሱ መቅረብ እንደምንፈልግ ያሳያል። አምላክም ቢሆን “በስሙ ላይ ለሚያሰላስሉ [ወይም “ስሙን ከፍ አድርገው ለሚመለከቱ” የግርጌ ማስታወሻ]” ሰዎች ልዩ ትኩረት ይሰጣል!—ሚልክያስ 3:16

አምላክን ለማወቅ ልንወስደው የሚገባን የመጀመሪያውና ወሳኙ እርምጃ ስሙን ማወቅ ነው። ሆኖም ይህ ብቻ በቂ አይደለም። ስሙ የሚወክለው አካል ምን ባሕርያት እንዳሉት ማወቅም ይኖርብናል።

የአምላክ ስም ማን ነው? የአምላክ ስም ይሖዋ ነው። ይህ ስም አምላክ ዓላማውን ዳር የማድረስ ችሎታ ያለው አካል እንደሆነ ያሳያል

አምላክ ከየት መጣ?

ይህ ብዙ ሰዎችን ሲያሳስብ የኖረ ጥያቄ ነው። ምናልባት አንተም ይህ ጥያቄ ተፈጥሮብህ ያውቅ ይሆናል። ይህን ጥያቄ በሌላ አባባል እንዲህ ብለን ልናስቀምጠው እንችላለን፦ ጽንፈ ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ወደ ሕልውና ያመጣው አምላክ ከሆነ አምላክ ራሱ ከየት መጣ?

በጥቅሉ ሲታይ ሳይንቲስቶች፣ ግዑዙ ጽንፈ ዓለም መጀመሪያ እንዳለው ይስማማሉ። ከዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ጋር በሚስማማ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘው የመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር “በመጀመሪያ አምላክ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ” ይላል።—ዘፍጥረት 1:1

ጽንፈ ዓለም፣ ራሱን በራሱ ሊፈጥር አይችልም። ምክንያቱም ጽንፈ ዓለም ራሱን ፈጠረ ማለት ከሌለ ነገር መጣ ማለት ነው። ሆኖም የሌለ ነገር፣ ለአንድ ነገር መገኘት ምክንያት ሊሆን አይችልም። ጽንፈ ዓለም ወደ ሕልውና ከመምጣቱ በፊት ምንም ነገር ካልነበረ ዛሬ ጽንፈ ዓለም ራሱ ሊኖር አይችልም ነበር። ሐሳቡን ሙሉ በሙሉ መረዳት ቢከብደንም ጽንፈ ዓለም ወደ ሕልውና እንዲመጣ ከተፈለገ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የሌለው ብሎም ግዑዝ ከሆነው ጽንፈ ዓለም ውጭ የሆነ አካል የግድ መኖር አለበት። ይህ አካል ገደብ የለሽ ኃይልና ጥበብ ያለው እንዲሁም መንፈስ የሆነው ይሖዋ አምላክ ነው።—ዮሐንስ 4:24

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ ሲናገር “ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም አንተ አምላክ ነህ” ይላል። (መዝሙር 90:2) ስለዚህ አምላክ ምንጊዜም ነበረ ማለት ነው። ከዚያም “በመጀመሪያ” ግዑዙን ጽንፈ ዓለም ፈጠረ።—ራእይ 4:11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ