JW.ORG ላይ የወጡ ርዕሶች
ቀደም ሲል መጽሔቶቻችን ላይ ይወጡ የነበሩ ቋሚ ዓምዶች አሁን jw.org በተባለው ድረ ገጻችን ላይ መውጣት ጀምረዋል፤ ከዚህ እትም ጀምሮ መጠበቂያ ግንብ በእነዚህ ቋሚ ዓምዶች ሥር የሚወጡትን አዳዲስ ርዕሶች ያስተዋውቃል።
ለቤተሰብ
በቁጣ መገንፈል ጤናን ይጎዳል፤ ሆኖም ቁጣን አምቆ መያዝም ጉዳት ያስከትላል። የሚያበሳጩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟችሁ ቁጣችሁን መቆጣጠር የምትችሉት እንዴት ነው?
(የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ትዳር እና ቤተሰብ በሚለው ሥር ይገኛል።)
መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል
አንቶኒዮ በዕፅና በአልኮል ሱስ እንዲሁም በዓመፅ የተጠላለፈ ሕይወት መምራቱ ሕይወት ምንም ዓላማ እንደሌለው እንዲሰማው አድርጎታል። አመለካከቱን እንዲቀይር ያደረገው ምንድን ነው?
(የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ሰላም እና ደስታ በሚለው ሥር ይገኛል።)