ማስታወቂያዎች
◼ በአገልግሎት የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በነሐሴ፦ ከሚከተሉት ብሮሹሮች ማንኛውንም ማበርከት ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ”፣ በሥላሴ ማመን ይኖርብሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ ወይም የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች። በመስከረም፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ።
◼ ጉባኤዎች የ1994 የይሖዋ ምስክሮች የቀን መቁጠሪያ ምን ያህል እንደሚፈልጉ ከመስከረም የጽሑፍ ጥያቄ ጋር መላክ ሊጀምሩ ይችላሉ።
◼ እያንዳንዱ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18) ይላኩለታል። የጉባኤው ጸሐፊና የጽሑፍ አገልጋዩ በነሐሴ መጀመሪያ ላይ ተገናኝተው በወሩ መጨረሻ ላይ በጉባኤው እጅ ያሉትን ጽሑፎች የሚቆጥሩበትን ቀን ለመወሰን መነጋገር አለባቸው። በጉባኤው እጅ ያሉትን ጽሑፎች ሁሉ እቦታው ድረስ ሄደው መቁጠር አለባቸው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉትን መጽሔቶች ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ ማግኘት ይቻላል። እባካችሁ ከመስከረም 6 ሳታሳልፉ ዋናውን ቅጂ ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ በፋይላችሁ ውስጥ አስቀሩ። ሦስተኛው ቅጂ እንደ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጸሐፊው ቆጠራው ትክክል መሆኑን ሊቆጣጠርና የተሞላውም ቅጽ በመሪ የበላይ ተመልካቹ ተመርምሮ ሊፈረምበት ይገባል።
◼ ለ1994 የአገልግሎት ዓመት የሚያገለግሉ በቂ ቅጾች ለየጉባኤዎች እየተላኩ ናቸው። እነዚህ ቅጾች ሊባክኑ አይገባም። ልትጠቀሙባቸው የሚገባችሁ ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
◼ ከጉባኤው ጋር ግንኙነት ያለው ማንኛውም ሰው የግሉ የሆነ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች አዲስ ኮንትራት ለመግባትም ሆነ የበፊቱን ለማደስ ከፈለገ ይህንን ማድረግ የሚችለው በጉባኤው በኩል ነው።
◼ አስፋፊዎች ጽሑፍ ለማግኘት በግላቸው የሚያቀርቡትን ጥያቄ ማኅበሩ አያስተናግድም። ጽሑፍ ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ሊነግሩት ይችላሉ። እርሱም የተፈለገውን ጽሑፍ በጉባኤው የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ ውስጥ ይጨምረዋል። መሪ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ የጉባኤውን ወርኀዊ የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ለማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግላቸው ጽሑፍ ለማግኘት የሚፈልጉ የጽሑፍ አገልጋዩን እንዲያነጋግሩት የሚገልጽ ማስታወቂያ ይናገራል።
◼ መስከረም 1 ቀን 1993 የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ለመጀመር ዕቅድ ያላቸው አስፋፊዎች ሳይዘገዩ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ማመልከቻዎቹ የነሐሴ ወር ከማለቁ በፊት ለማኅበሩ መላክ ይገባቸዋል። የ9–68 መንግሥት አገልግሎታችን ን ተጨማሪ ክፍል ገጽ 6 አንቀጽ 21 እስከ 26 እባካችሁ እንደገና ተመልከቱት።
◼ የጉባኤው ጸሐፊ የአገልግሎት ሪፖርቱን አዘጋጅቶ በጉባኤ የምርመራ ሪፖርት ቅጽ (S-10) ላይ ይመዘግበዋል። እንዲሁም ሪፖርቶችን የሚያዘጋጀውን ሽማግሌ ወይም ዲያቆን ምን ማድረግ እንዳለበት በጥንቃቄ መመሪያ ይሰጠዋል። ይህም ከጉባኤ አስፋፊ ካርዶች (S-21) ላይ የሚያስፈልገውን ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ይረዳል። የጉባኤ ምርመራ ሪፖርት (S-10) በትክክልና በንጽሕና መሞላትና በአገልግሎት ኮሚቴው በጥንቃቄ መመርመር ይኖርበታል።
◼ ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር የተባለው ቡክሌት ከመታተሙ በፊት ለጉባኤያችሁ ምን ያህል ብዛት እንደሚያስፈልገው ወስናችሁ ላኩልን።
◼ ባለ ቀለም የአማርኛ መጠበቂያ ግንብ መጽሔት ለጉባኤያችሁ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ያልገለጻችሁ ጉባኤዎች እባካችሁ ቶሎ ግለጹልን። ትዕዛዝ ያልላከ ጉባኤ መጽሔቱ አይመጣለትም።
◼ የጽሑፍ ዋጋ:- (ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ጥናት 20–38) ብር 1.20