የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/94 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 3/94 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- መጋቢት፦ ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! ወይም የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው ሚያዝያ እና ግንቦት:- የመጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባት። ሰኔ:- ሕይወት እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት? ማሳሰቢያ:- ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ጊዜ በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S–14–AM) ላይ ማዘዝ ይችላሉ።

◼ ከጉባኤው ጋር የሚሰበሰብ እያንዳንዱ ሰው በግሉ የሚገባቸውን ኮንትራቶች ጨምሮ አዲስ የመጠበቂያ ግንብ ወይም ንቁ! ኮንትራት መግባትም ይሁን የነበረውን ማሳደስ የሚችለው በጉባኤው በኩል ነው።

◼ መሪ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው መጋቢት 1 ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ውጤቱን ለጉባኤው አስታውቁ።

◼ በኢትዮጵያ የአካባቢ የሕንፃ ሥራ ኮሚቴ መቋቋሙን ስናሳውቃችሁ ደስ ይለናል። በታኅሣሥ 1993 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጣው ሐሳብ ጋር በመስማማት የመንግሥት አዳራሽ የግንባታ ወይም የማሻሻያ ፕሮጀክት የሚያካሂዱ ጉባኤዎች በሙሉ በሚከተለው አድራሻ ይህንን ኮሚቴ ማማከር ይኖርባቸዋል:- ለአካባቢ የሕንጻ ሥራ ኮሚቴ፤ ፖ.ሣ.ቁ 40023፤ አዲስ አበባ። በዚህ ኮሚቴ ውስጥ በፈቃደኝነት ለማገልገል የሚፈልጉ ልዩ የግንባታ ችሎታ ያላቸው ወንድሞችም ይህንን ፍላጎታቸውን በዚህ አድራሻ ወይም ለክልል የበላይ ተመልካቻቸው ሊገልጹ ይችላሉ። በሌሎች አገሮች ውጤታማ ሆኖ የተገኘው ይህ ግሩም ዝግጅት በአገራችን ውስጥ የሚያስፈልጉትን የመንግሥት አዳራሾች በመገንባት ትልቅ ድርሻ እንደሚያበረክት ከልብ ተስፋ እናደርጋለን።

◼ በዚህ ዓመት ከሐምሌ እስከ መስከረም በገለልተኛ ክልሎች በሚደረገው ዘመቻ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ በመሆን ለማገለገል የሚፈልጉ የዘወትር አቅኚዎች በጉባኤያቸው የሽማግሌዎች አካል (ወይም የአገልግሎት ኮሚቴ) በኩል ሊያመለክቱ ይችላሉ። የአገልግሎት ኮሚቴዎች ግለሰቡ ጊዜያዊ ልዩ አቅኚ መሆኑን ለምን እንደሚደግፉ፤ እንዲሁም አቅኚው ወይም አቅኚዋ ነጠላ ወይም ባለትዳር፣ ወንድ ወይም ሴት መሆናቸውን (ልጆች ካሏችው ብዛታቸውን) እና አመልካቹ ለየትኛውም ጉባኤ ባልተመደበ የአገልግሎት ክልል ውስጥ ለሦስት ወራት ያህል ቢመደብ ለመሄድ የሚችል መሆኑን እንዲጠቅሱ ይጠየቃሉ። የአገልግሎት ኮሚቴዎች እነዚህን ነጥቦች በግልጽ በማስቀመጥና አስተያየታቸውን አክለው የግለሰቡን ማመልከቻ ግፋ ቢል እስከ ሚያዝያ 15 ድረስ ለማኅበሩ መላክ አለባቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ