የመጋቢት የአገልግሎት ስብሰባዎች
መጋቢት 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “ወጣትነትህ የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ” የሚለውን ርዕስ በአጭሩ ተወያዩበትና ተስማሚ ሆኖ ሲያገኙት መጽሐፉን እንዲጠቀሙበት አስፋፊዎችን አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “ለሕዝብ የምትሰጡትን የተስፋችሁን ምሥክርነት ሳትወላውሉ አጽንታችሁ ያዙ” በመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪ በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። በስብሰባ ላይ ሐሳብ ለመስጠት የነበረባቸውን ፍርሃት የተወጡት አስተያየት እንዲሰጡ አድርግ። አስቀድሞ የመዘጋጀትን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ። በየሳምንቱ የጉባኤ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት ሲደረግ ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ እንዲዘጋጁ ጉባኤውን አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ስሜት ቀስቃሽ መልእክት አውጅ።” ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ጥሩ ዝግጅት ያደረጉ አስፋፊዎች ከአንቀጽ 2–4 ላይ ያሉትን አቀራረቦች በትዕይንት እንዲያሳዩ አድርግ። ከእያንዳንዱ ትዕይንት በኋላ ከአቀራረቡ ስላገኙት ትምህርት ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ። በዚህ ወር ሁሉም የራእይ መደምደሚያ የተባለውን መጽሐፍ እንዲያበረክቱ አበረታታቸው።
መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 14 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሰያዊ ዜናዎች። በዚህ ሳምንት ለሚደረገው የመስክ አገልግሎት ሊያገለግል በሚችል በቅርብ ጊዜ በወጡ መጽሔቶች ላይ ባለ ነጥብ ላይ እንዲያተኩሩ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ “ለይሖዋ የምታቀርበውን ምስጋና በሚያዝያ ወር ከፍ ልታደርገው ትችላለህን?” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። ቀደም ሲል ረዳት አቅኚ ሆነው የነበሩት አስተያየት እንዲሰጡ አድርግ። ከዚህ መብት ለመጠቀም ሲሉ እንዴት ጉዳዮቻቸውን እንዳስተካከሉ እንዲያስረዱ ጠይቃቸው። በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ለመሆን ያሰቡትን በተቻለ መጠን ቶሎ ማመልከቻውን ሞልተው እንዲመልሱ አበረታታቸው።
20 ደቂቃ፦ “በመታሰቢያው በዓል ላይ ጥሩ አቀባበል አድርጉላቸው።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። አንቀጽ 3ን ካብራራህ በኋላ አንድ ዲያቆን ለመታሰቢያው በዓል የመጣን አንድ አዲስ ሰው ሲቀበል የሚያሳይ አጭር ትዕይንት አቅርብ።
መዝሙር 105 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 215
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች፤ እንዲሁም የሒሳብ ሪፖርት፤ ማኅበሩ የተላከለት መዋጮ እንደደረሰው ያሳወቀበት ደብዳቤ ካለ ጨምረህ አቅርብ። “በተገቢው ጊዜ የሚቀርብ ምግብ” በሚል ርዕስ በሣጥኑ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ተወያዩበት። ሚያዝያ 10 ለሚሰጠው ልዩ ንግግር ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች እንዲጋብዙ ሁሉንም አበረታታ።
20 ደቂቃ፦ “መልእክቱን ተቀብለው እርምጃ እንዲወስዱ እርዳቸው።” በውይይት የሚቀርብ። በአንቀጽ 2 እና 3 ላይ ባሉት አቀራረቦች በመጠቀም ጥሩ ዝግጅት የተደረገባቸው ትዕይንቶች አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ ከመታሰቢያው በዓል ጋር በተያያዘ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። “ለመታሰቢያው በዓል የሚደረግ ዝግጅት” በሚለው በመጋቢት 1993 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 7 ላይ የወጣውን የመሳሰሉ ጠቃሚ ትምህርቶችን ከልሱ።
መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መጋቢት 28 የሚጀምር ሳምንት
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በየካቲት ወር የምናበረክታቸውን መጻሕፍት በመጠቀም በክልላችሁ ውስጥ ለማገልገል ተስማሚ የሆኑትን መንገዶች በውይይትና በትዕይንት አቅርብ። አንዳንድ አስፋፊዎች እንዴት የመጽሔት ኮንትራት ሊያስገቡ እንደቻሉ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን ተናገር።
15 ደቂቃ፦ አንድ ሽማግሌ ከ1994 የዓመት መጽሐፍ ውስጥ ከገጽ 19–32 ላይ ስለ ዓለም አቀፉ የመንግሥት ሥራ መስፋፋት ከሚናገረው ክፍል በተመረጡ ጎላ ያሉ ነጥቦች ላይ በማተኮርና ለዚህ ጉባኤው ያደረገውን ድጋፍ የሚያሳዩ ገንቢ ጐኖችን በማጉላት ይጠቅሳል። ይሖዋ በአቅም ማነስ ሳቢያ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር የተገደበባቸውን ጨምሮ ሕዝቦቹን እንዴት አትረፍርፎ እየባረከ እንዳለ ግለጽ። ጉባኤው የዓመቱ መጽሐፍ ካልደረሰው ይህን ክፍል በቅርብ ጊዜ ከክልል የበላይ ተመልካቹ ጉብኝት የተገኙትን አንዳንድ ነጥቦች በመከለስ ወይም ከወረዳ ስብሰባ የተገኙትን አንዳንድ ዋና ዋና ነጥቦች በመከለስ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
15 ደቂቃ፦ የ“በጎ ስጦታ ሁሉ” ሰጭ። በታኅሣሥ 1, 1993 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 28–31 ላይ የተመሠረተ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።