የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሚያዝያ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “እውነተኛው ሃይማኖት ለሰብአዊው ኅብረተሰብ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ያሟላል” በሚል ርዕስ ሚያዝያ 10 ስለሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር ሁሉንም አሳስብ። ሕዝብ ንግግሩ ሲሰጥ አዲሶች እንዲገኙ ለመርዳት ልዩ ጥረት ሊደረግ ይገባል።
15 ደቂቃ፦ “መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ለእውነት የቆሙ መጽሔቶች”። በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። አድማጮች የሚያበረክቱትን የመጽሔት ቁጥር ከፍ ለማድረግ የተጠቀሙባቸውን ዘዴዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። ጊዜ ካለ አንዳንድ ተሞክሮችን ተናገር።
20 ደቂቃ፦ “በዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ የሌላቸውን መጽሔቶች አበርክት።” ከአድማጮች ጋር በመወያየት ትምህርቱን አቅርብ። መጽሔቶቹ የሚሰጡትን ልዩ ጥቅም አጉላ። አንቀጽ 2ን በምታብራራበት ጊዜ አንድ ውጤታማ አስፋፊ መጽሔቶቹ ከያዟቸው ትምህርቶች ጋር እንዴት እንደሚተዋወቅና ለማበርከት እንዴት እንደሚዘጋጅ እንዲያስረዳ ጠይቅ። የሚያዝያ 1 እና 15 ወይም በቅርብ የወጡትን እትሞች ማበርከት የሚቻልባቸውን መንገዶች የሚያሳዩ ሁለት ትዕይንቶች አዘጋጅ። በቅርብ ጊዜ የወጡትን የንቁ! እትሞች ለማበርከት በሚረዱ ርዕሶች ላይ ሐሳብ በመስጠት ደምድም።
መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት
ሚያዝያ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 191
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። በጥያቄ ሣጥኑ ውስጥ ያሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራራ።
15 ደቂቃ፦ “የአገልግሎት ስብሰባ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተሟላ ብቃትና ዝግጅት እንዲኖረን ያስችለናል።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። አንድ ቤተሰብ ለስብሰባ እንዴት እንደሚዘጋጅ የሚያሳይ ትዕይንት በማቅረብ (1) አስቀድሞ የመዘጋጀት፣ (2) በጥሞና የማዳመጥና (3) የመሳተፍን አስፈላጊነት አጉላ።
20 ደቂቃ፦ “በሌሎች ነገሮች ሳትባክን ይሖዋን አገልግል” አባሪ ሆኖ የወጣውን ትምህርት በጥያቄና መልስ አቅርብ። ከ1 እስከ 6 ድረስ ያሉትን አንቀጾች ሸፍን።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 85
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የተላከለት መዋጮ የደረሰው መሆኑን ገልጾ ከሆነ ይህን ጨምረህ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “ጽሑፍ የተበረከተላቸውን ሰዎች ሁሉ ተከታትለህ እርዳ” ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚሸፈን። በመጽሔቶቹ ውስጥ ካሉት ትምህርቶች ጋር በደንብ መተዋወቅና ከሁሉ የተሻለው አቀራረብ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ባለፈው ጊዜ የቤቱ ባለቤት ያሳየውን ምላሽ በጥንቃቄ መመርመር ያለብን ለምን እንደሆነ አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ችሎታ ያላቸው አስፋፊዎች በቀረቡት ሐሳቦች ላይ ትዕይንት እንዲያሳዩ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “በሌሎች ነገሮች ሳትባክን ይሖዋን አገልግል” አባሪ ሆኖ የወጣውን ትምህርት በጥያቄና መልስ አቅርብ። ከ7 እስከ 12 ድረስ ያሉትን አንቀጾች ሸፍን።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሚያዝያ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 53
10 ደቂቃ፦ የጉባኤው ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ እምነት። ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 129–32 ላይ የተመሠረተ። በአንድ ሽማግሌና በወጣቶች መካከል የሚደረግ ውይይት። ሽማግሌው የእምነትን ትርጉም ካብራራ በኋላ ለወጣቶቹ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ያቀርብላቸዋል:- ብዙዎች እምነት የሌላቸው ለምንድን ነው? የእምነታችን መሠረቱ ምንድን ነው? ጠንካራ እምነት እንደያዝን ለመኖር የምንችለው እንዴት ነው? እንዲህ ያለውን እምነት በሥራ ልናሳይ የምንችለውስ እንዴት ነው? ሽማግሌው ወጣቶቹን በማመስገንና በማበረታታት ይደመድማል።
20 ደቂቃ፦ “ንጽሕና አምላክን ያስከብራል።” አንድ ሽማግሌ ትምህርቱን ከአድማጮች ጋር ይወያይበታል። በ11–110 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 15–20 ላይ የተሰጡትን ምክሮች የሚከልስ አጠር ያለ ንግግር በማቅረብ ደምድም።
መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት