የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሐምሌ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 191
10 ደቂቃ፡- የጉባኤው ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ተስማሚ የሆኑ ማስታወቂያዎች። ጉባኤው ያሉትን የቆዩ መጽሐፎች አርእስት ጥቀስ፤ አስፋፊዎች መጽሐፎቹን ወስደው ለአገልግሎት እንዲጠቀሙባቸው አበረታታ።
17 ደቂቃ፡- “ያለማሰለስ ከቤት ወደ ቤት መሄድ።” ጥያቄና መልስ። ከአድማጮች ውስጥ ከበር ወደ በር በሚደረገው ሥራ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ ከምሥክሮቹ ጋር የተገናኙ አንዳንዶች ያላቸውን አድናቆት እንዲገልጹ ጋብዝ።
18 ደቂቃ፡- “ሌሎች እውነትን እንዲማሩ እርዳቸው።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ጥሩ ችሎታ ያላቸው አስፋፊዎች በክፍሉ ላይ የተሰጡትን ሁለት ወይም ሦስት አቀራረቦች በትዕይንት እንዲያቀርቡ አድርግ። አጭርና ቀልጠፍ ያለ አቀራረብ ጥሩ መሆኑን አጥብቀህ ግለጽ።
መዝሙር 105 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 121
12 ደቂቃ፡- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ ለተላከለት መዋጮ ያቀረበው ምስጋና ካለ ጨምረህ አንብብ። ለተደረገው መዋጮ ምስጋና አቅርብ።—ዘጸ. 35:29
15 ደቂቃ፡- አስፋፊዎች ከሽማግሌዎችና ከሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴ ጋር መተባበር እንዳለባቸው የሚገልጸውን ግንቦት 1, 1994 የተላከውን የማኅበሩን ደብዳቤ አንብብና አብራራ። እምነትን የሚፈታተን የሕክምና አሰጣጥ በሚያጋጥምበት ጊዜ በዚህ ደብዳቤ ላይ የተዘረዘሩትን ሥርዓቶች መከተል እንደሚገባ አጥብቀህ ግለጽ። በደብዳቤው ላይ የተጠቀሱትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በማንበብ ደምድም። በተለይ በአንቀጽ 2 እና 6 ላይ አተኩር።
18 ደቂቃ፡- “ቤታቸው ሄደን ካላነጋገርናቸው እንዴት ይሰማሉ?” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት።
መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
15 ደቂቃ፡- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በተጨማሪም “መጽሐፍ ቅዱስ—በጥንታዊነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ዘመናዊ የሰው ልጆች መጽሐፍ” የሚለውን ርዕስ በጥያቄና መልስ ሸፍን። ቅዳሜና እሁድ ለመስክ አገልግሎት የተደረጉትን ዝግጅቶች ግለጽ። እንዲሁም መጽሔት በማሠራጨቱ ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታቸው።
8 ደቂቃ፡- የጥያቄ ሣጥን። በጥያቄና መልስ ተወያዩበት።
22 ደቂቃ፡- “ውጤታማ በሆነ የመንገድ ላይ ምሥክርነት አማካኝነት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ማግኘት።” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ወይም በመንገድ ላይ ምሥክርነት ውጤታማ የሆነ ሌላ ብቁ የሆነ ሽማግሌ በመንገድ ላይ ምሥክርነት የመስጠት ልምድ ካላቸው ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ጋር በትምህርቱ ላይ ይወያይበት። በቅርብ ጊዜ የወጡትን መጽሔቶች ማበርከት የሚቻልባቸውን አቀራረቦች በትዕይንት አሳይ።
መዝሙር 174 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 53
10 ደቂቃ፡- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። በቅርብ ጊዜ የወጡ መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል በትዕይንት አሳይ። መጽሔት በማሠራጨቱ ሥራ ሁሉም እንዲካፈሉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፡- “ትንንሽ ልጆች መልካም ምሳሌ ያስፈልጋቸዋል።” ጥያቄና መልስ። ጥሩ አርዓያ ከሆኑ አንድ ወይም ሁለት ወጣቶች ጋር ቃለ ምልልስ አድርግ። ምን ምን መንፈሳዊ ግቦች እንዳወጡና የሚያደርጉት ጥረት ምን ተጨማሪ በረከት እንዳመጣላቸው እንዲገልጹ አድርግ።
20 ደቂቃ፡- የአቀራረባችንን ውጤታማነት ማሻሻል። አንድ ቤተሰብ በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ጥናት 19 አንቀጽ 9 ላይ በተሰጡት ሐሳቦች ላይ የተመሠረተ ልምምድ ያደርጋል። ከቤተሰቡ አባላት አንዱ አንድ የአቀራረብ መንገድ ያሳያቸዋል፤ ሌሎቹም አቀራረቡን ያደንቁና የማሻሻያ ሐሳቦች ያቀርቡለታል። እንዲሁም በአካባቢያችሁ የሚያጋጥም የተለመደ ተቃውሞ ይግለጹና ያንን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል ይወያዩበት።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።