የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/94 ገጽ 11
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 8/94 ገጽ 11

ማስታወቂያዎች

◼ ከሐምሌ እስከ መስከረም፦ በጉባኤ ወይም በግል የሚገኙ ቀለሙ እየለቀቀ በሚሄድ ወረቀት የታተሙ የቆዩ መጻሕፍት እንደ ታላቁ አስተማሪ እንዲሁም ዘላለማዊ ዓላማ፣ ሕይወት ይህ ብቻ ነውን?፣ መንፈስ ቅዱስ፣ የሰው ልጅ መዳንና የሺህ ዓመት ግዛት የተባሉትን የእንግሊዝኛ መጻሕፍት በአንድ ብር ማበርከት ይቻላል። የጉባኤዎቹ ጸሐፊዎች በአስፋፊዎች ወይም በአቅኚዎች የተወሰዱትን መጻሕፍት በቅጽ S–20–AM ላይ የዋጋ ልዩነት እንዲቀነስላቸው መጠየቁን መዘንጋት የለባቸውም። በተጨማሪም አረንጓዴ ቀለም ያለው የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም በ5 ብር ሊበረከት ይችላል። መስከረም፦ ከላይ የተገለጹት የቆዩ መጻሕፍት ካለቁ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፍ ልናበረክት እንችላለን። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱት የዘመቻ ጽሑፎች የሚያስፈልጓቸው ጉባኤዎች በሚቀጥለው ጊዜ በሚልኩት ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ (S–14–AM) ላይ ማዘዝ ይችላሉ።

◼ በትእዛዝ ልታገኟቸው የምትችሏቸው ጽሑፎች:- የ1994 የቀን መቁጠሪያ (በእንግሊዝኛ)፣ የትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ (በእንግሊዝኛ)፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች (በአማርኛ)

◼ ለ1995 የአገልግሎት ዓመት የሚያገለግሉ በቂ ቅጾች ለየጉባኤው እየተላኩ ናቸው። እነዚህ ቅጾች እንዲሁ መባከን አይገባቸውም። ለታቀደላቸው ዓላማ ብቻ መዋል ይኖርባቸዋል።

እያንዳንዱ አስፋፊ ኮንትራት ስለማስገባት ማብራሪያ የሚሰጠው S-11-AM የተባለ ቅጽ ሊደርሰው ይችላል። የመታሰቢያው በዓል ሪፖርት የሚሞላበት አረንጓዴ ቀለም ያለው S-7-AM የተባለው ቅጽ ከበዓሉ በኋላ እንዲሠራበት በጥሩ ሁኔታ መቀመጥ አለበት። የእነዚህ ቅጾች ሒሳብ በወርኃዊ ሒሳብ መጠየቂያ ላይ ሲመጣ ከጉባኤው ወጪ ተደርጎ የሚከፈል ይሆናል።

◼ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም:- ከጥቅምት 21–23 1994 በአዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም ይደረጋል።

◼ ከጉባኤው ጋር የሚሰበሰብ እያንዳንዱ ሰው በግሉ የሚገባቸውን ኮንትራቶች ጨምሮ አዲስ የመጠበቂያ ግንብ ወይም ንቁ! ኮንትራት መግባትም ይሁን የነበረውን ማሳደስ የሚችለው በጉባኤው በኩል ነው።

◼ ማኅበሩ ግለሰብ አስፋፊዎች የሚልኩትን የሥነ ጽሑፍ ጥያቄ አይቀበልም። አንድ ዓይነት ጽሑፍ የሚፈልጉ አስፋፊዎች የጉባኤያቸውን የሥነ ጽሑፍ አገልጋይ ሊጠይቁት ይችላሉ። እርሱም ሳይዘገይ በጉባኤው ወርኃዊ የሥነ ጽሑፍ መጠየቂያ ውስጥ ሊጨምረው ይችላል። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ መጠየቂያ ለማኅበሩ ከመላኩ በፊት መሪ የበላይ ተመልካቹ በግል ጽሑፎችን ለማግኘት የሚፈልጉ ካሉ ለሥነ ጽሑፍ አገልጋዩ ሊነግሩት እንደሚችሉ በየወሩ በማስታወቂያ እንዲነገር ማድረግ ይኖርበታል።

እያንዳንዱ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጾች (S-18–AM) ይላኩለታል። የጉባኤው ጸሐፊና የጽሑፍ አገልጋዩ በነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች የሚቆጠሩበትን ቀን ለመወሰን በወሩ መጀመሪያ ላይ ተገናኝተው መነጋገር አለባቸው። በጉባኤው እጅ ያሉት ጽሑፎች ሁሉ ባሉበት ቦታ በትክክል መቆጠር አለባቸው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር በጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉትን ጠቅላላ የመጽሔቶች ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ ማግኘት ይቻላል። እባካችሁ ከመስከረም 6 ሳታሳልፉ ዋናውን ቅጂ ለማኅበሩ ላኩ። አንድ የካርቦን ቅጂ በፋይላችሁ ውስጥ አስቀሩ። ሦስተኛው ቅጂ እንደ ጊዜያዊ መሥሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ጸሐፊው ቆጠራው ትክክል መሆኑን መቆጣጠር ይኖርበታል፤ የተሞላውም ቅጽ በመሪ የበላይ ተመልካቹ መመርመር አለበት። በቅጹም ላይ ጸሐፊውና መሪ የበላይ ተመልካቹ ይፈርሙበታል።

◼ መስከረም 1 ቀን 1994 የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ለመጀመር ዕቅድ ያላቸው አስፋፊዎች ሳይዘገዩ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

◼ የጉባኤው ጸሐፊ የአገልግሎት ሪፖርቱን አዘጋጅቶ በጉባኤ አናሊስስ ሪፖርት ቅጽ (S-10–AM) ላይ ይመዘግበዋል። እንዲሁም ሪፖርቶችን ለማጠናቀር የሚረዳውን ሽማግሌ ወይም ዲያቆን ምን ማድረግ እንዳለበት በጥንቃቄ መመሪያ ይሰጠዋል። ይህም ከጉባኤ አስፋፊ ካርዶች (S-21-AM) ላይ የሚያስፈልገውን ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ይረዳል። የጉባኤ አናሊስስ ሪፖርት (S-10-AM) በትክክልና በንጽሕና መሞላትና በአገልግሎት ኮሚቴው በጥንቃቄ መመርመር ይኖርበታል። ባለፉት ጊዜያት አንዳንድ ጉባኤዎች ይህን ቅጽ የላኩልን ዘግይተው ነው። እስከ መስከረም 6, 1994 ባለው ጊዜ ውስጥ ቅጹን ሞልታችሁ ብትልኩልን ለሥራችን መቀላጠፍ በጣም ይረዳናል።

◼ ከመስከረም 1, 1994 ጀምሮ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ቅርንጫፍ ቢሮ የሚከፈት መሆኑን ስናስታውቃችሁ ደስ ይለናል። የናይሮቢ ቅርንጫፍ ቢሮ ለብዙ ዓመታት ጥሩ አገልግሎት ሰጥቶናል። አሁን ደግሞ እዚህ ቅርብ ሆነን ከእናንተ ጋር በቀጥታ በመገናኘት አስፈላጊውን ትኩረት እንደምንሰጣችሁ ተስፋ እናደርጋለን። ስለዚህ ከመስከረም ጀምራችሁ ደብዳቤዎቻችሁን:- የይሖዋ ምሥክሮች፤ ፖ.ሣ.ቁ 5522፤ አዲስ አበባ በማለት ትልኩልናላችሁ ማለት ነው።

◼ የመስክ አገልግሎት ሪፖርትን ስለመመለስ የወጣውን ዝግጅት ለማሻሻል አስፋፊዎችም ሆኑ አቅኚዎች ከአሁን ወዲያ የአገልግሎት ሪፖርታቸውን ወሩ በገባ በ25ኛው ቀን በመመለስ ፋንታ በወሩ የመጨረሻ ቀን ላይ ለጉባኤው እንዲመልሱ እናሳስባለን። ከዚያም ፀሐፊው የጉባኤውን ሪፖርት በቀጣዩ ወር እስከ 6ኛው ቀን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ እኛ ይልከዋል።

◼ ከኢንሹራንስ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የመንግሥት አዳራሽ ሥራ መርጃ የተባለ ዝግጅት አሁን የተጀመረ መሆኑንና የራሱ አዳራሽ ያለው ወይም የስብሰባ አዳራሽ የተከራየ ማንኛውም ጉባኤ ሊጠቀምበት እንደሚችል እናስታውቃችኋለን። ዝግጅቱ ተሠርተው ላላለቁ የመንግሥት አዳራሾችም ሆነ በመሰብሰቢያ አዳራሾች ውስጥ ለሚገኙ ንብረቶች የሚያገለግል ነው። የዚህ ዝግጅት ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚፈልጉ ጉባኤዎች ሁሉ ደብዳቤ በመጻፍ ሊያስታውቁን ይችላሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ