የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/94 ገጽ 2
  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 1 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 15 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 22 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 29 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 8/94 ገጽ 2

የነሐሴ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ነሐሴ 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 155

12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተወሰዱ ተስማሚ ማስታወቂያዎች። በቅርብ ታትመው ከወጡት መጽሔቶች ውስጥ በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረገው የመስክ አገልግሎት ላይ ጎላ ተደርገው ሊቀርቡ የሚችሉትን የመነጋገሪያ ነጥቦች በትዕይንት አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “አዎንታዊ አመለካከት ያዙ።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ ያሉት ሰዎች ግድየለሾችና ተቃዋሚዎች ቢሆኑም እንኳ አዎንታዊ አመለካከት እንደያዘ እንዲቀጥል የረዳው ነገር ምን እንደሆነ ሊናገር ከሚችል አንድ አቅኚ ወይም ለረጅም ጊዜ አስፋፊ ሆኖ ካገለገለ ሌላ ሰው ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ።

18 ደቂቃ፦ “አካላዊ ንጽሕና ይሖዋን ያስከብራል” “አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት” በተባለው መጽሐፍ ላይ ከገጽ 68–69 (ወይም 130–131) ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። የታይፎይድና የኮሌራ በሽታዎች መስፋፋታት ይህን ጉዳይ ለእኛ ይበልጥ አስፈላጊ እንዳደረገው ግለጽ። በአጠቃላይ ሲታይ አሁን ለሳሙናና ለቀለም የምናወጣው ወጪ በኋላ ለመድኃኒትና ለሐኪሞች ከምንከፍለው ገንዘብ ያነሰ እንደሆነ ጥቀስ። ከአንቀጽ 1 ጋር አያይዘህ ዘዳግም 23:11–14⁠ን አንብብና ስለ መጸዳጃ ቤቶች አጠቃቀምና ከተጠቀምን በኋላም እጃችንን የመታጠቡን አስፈላጊነት ተወያዩበት። አንቀጽ ሁለት ላይ ስትደርስ በሽታ ተሸካሚ የሆኑትን ነፍሳት ለመዋጋት በሁሉም አቅጣጫ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ጽዳት የማካሄድን አስፈላጊነት ጠቁም። ዘወትር መታጠብን አጠንክረህ ግለጽ። ልጆች ገላቸው ሲቆሽሽና ፊታቸውን ዝንብ ሲወራቸው ዝም ብሎ ማየት አይገባም። ምግብ ከመንካታችን በፊት እጆቻችንን በሳሙና መታጠብ ይኖርብናል። እንዲሁም የቤታችን ግድግዳዎች እንዳይቆሽሹ በሳሙና ሊታጠቡና ካስፈለገም ቀለም መቀባት ይኖርባቸው ይሆናል። አንቀጽ 3 ላይ ስትደርስ የሚታጠቡ ልብሶችን መክደኛ ባለው ዕቃ ወይም ቅርጫት ውስጥ ማስቀመጥንና በሰው ፊት ንጹሕ ሆነን መቅረብ የምንችልበት አቋም እንዲኖረን ልብሶችን አዘውትሮ ስለ ማጠብ ማበረታቻ ስጥ። ቅዱሳን በመሆን አሁን የምናገኛቸውን ጥቅሞችና በዚህ ረገድ ከቅዱሳን ጽሑፎች ምን እንደሚጠበቅብን ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። — 1 ጴጥ. 1:16

መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 53

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “ወንድሞቻችሁን በደንብ እወቋቸው።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አድማጮች በአንቀጽ 6 ላይ የተሰጡትን ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ እንዴት ሌሎችን በደንብ ለማወቅ እንደቻሉ የሚያሳይ አጭር ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።

20 ደቂቃ፦ “አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ”። አድማጮች ለዚህ ግሩም መጽሐፍ አድናቆት እንዲያድርባቸው ቀስቅስ። እንዲሁም ከገጽ 5–8 (ንዑስ ርዕስ ድረስ) ያለውን ተወያዩበት። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ዋና ዋናዎቹን ክፍሎች አንብባቸው።

መዝሙር 105 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 215

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች፤ እንዲሁም የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የተላከለት መዋጮ እንደደረሰው አሳውቆ ከሆነ ጨምረህ አቅርብ።

15 ደቂቃ፦ “አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ” በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 8–12 ያለውን ከጥቂት የክለሳ ጥያቄዎች ጋር አቅርብ።

25 ደቂቃ፦ “በሥርዓታማ ልማድ እያደጋችሁ መሄዳችሁን ቀጥሉ።” በጥያቄና መልስ የሚሸፈን።

መዝሙር 121 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

18 ደቂቃ፦ የ1994 “አምላካዊ ፍርሃት” የወረዳ ስብሰባ። ከአንቀጽ 1 እስከ 10 ያለውንና “የወረዳ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” የሚለውን ጨምረህ አቅርብ።

17 ደቂቃ፦ “ማደግህ ለሁሉም ግልጥ ሆኖ ይታይ።” ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አንዳንዶቹን አንቀጾች እያነበብክ በጥያቄና መልስ ሸፍነው።

መዝሙር 174 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 136

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ “እንደገና አቅኚ መሆን ትችል ይሆን?” ከአድማጮች ጋር በውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ እንደገና ወደ አቅኚነት አገልግሎት እንዴት ሊገባ አንደቻለ የሚያሳይ ወይም ከቤተሰቡ አባል አንዱ በዚህ መብት እንዲጠቀም ለመርዳት ቤተሰቡ እንዴት እንደተጋገዘ የሚያሳይ ከጉባኤው የተገኘ ተሞክሮ ጨምረህ አቅርብ።

13 ደቂቃ፦ የ1994 “አምላካዊ ፍርሃት” የወረዳ ስብሰባ። ከአንቀጽ 11 እስከ መጨረሻ ያለውን ሸፍን።

12 ደቂቃ፦ በመስከረም ወር በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ አበርክቱ። በመስከረም ወር ይህን መጽሐፍ ለማበርከትና ጥናት ለማስጀመር በጋለ ስሜት ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ። ይህ መጽሐፍ የወጣው በ1982 ሲሆን እስካሁን ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ላይ ዋነኛ ማስጠኛ ሆኖ ሲሠራበት ቆይቷል። በወረዳ ስብሰባው ላይ የተሰራጩት ቅጂዎች የሚከተለውን መልዕክት ይዘው ነበር:- “ይህ አዲስ ማሠልጠኛ መጽሐፍ ብዙ ሌሎች ሰዎች የእኛን ዓይነት ተስፋ እንዲይዙ ለመርዳት የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ ይዟል . . . አዲሶች ራሳቸውን ለይሖዋ ለመወሰንና ተቀባይነት ባለው መንገድ እርሱን ለማገልገል እንዲችሉ ማወቅ የሚያስፈልጓቸውን ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች አካትቷል።” በ1983 2,652,323 የነበረው የአስፋፊዎች ቁጥር በ1993 ወደ 4,709,889 በማደጉ የመጽሐፉ ጠቃሚነት በግልጽ ታይቷል። ይህንን መጽሐፍ በማጥናታቸው እውነትን እንዴት ለማወቅ እንደቻሉ ወይም ሌሎችን በዚህ መጽሐፍ በማስጠናታቸው እንዴት ሊረዷቸው እንደቻሉ ተሞክሯቸውን እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ