የመስክ አገልግሎት ስብሰባዎች
መስከረም 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 136
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጡት ማስታወቂያዎች ውስጥ ተስማሚዎቹን።
20 ደቂቃ፦ “ውድ ሀብት የሆነውን የመንግሥት አገልግሎትህን አስፋው።” የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹና ሌላ ሽማግሌ የትምህርቱን ዓበይት ነጥቦች ይወያያሉ። ያለፈውን ዓመት የጉባኤውን የአገልግሎት እንቅስቃሴ ከልስ፤ ከምስጋና ጋር የማሻሻያ ሐሳቦችን ስጥ። በግላችን የአገልግሎት እንቅስቃሴያችንን ከፍ ለማድረግ ግብ የማውጣትን አስፈላጊነት አጉላ።
15 ደቂቃ፦ “ሰዎች ለዘላለም መኖር ለተባለው መጽሐፍ ፍላጎት እንዲያድርባቸው አድርግ።” አንድ ወጣትን ጨምሮ ሦስት ወይም አራት አስፋፊዎች በትምህርቱ ላይ ይወያዩና ልምምድ ያደርጋሉ። ሁለት ወይም ሦስት ትዕይንቶችን አቅርበው እርስ በርስ ማሻሻያ ሐሳቦችንና ማበረታቻዎችን በመለዋወጥ ይከልሱታል።
መዝሙር 113 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 172
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ ክርስቲያኖች በትምህርት ቤት የሚያሳዩት ጠባይ። አንድ ሽማግሌ በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ካሉ ከሦስት ወይም ከአራት ወጣቶች ጋር የሚያደርገው ውይይት። ልጆቻችን በትምህርት ቤት ለመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓቶች ያላቸውን አክብሮት የሚቀንሱ ልዩ ልዩ ተጽዕኖዎች ያጋጥሟቸዋል። ከእነዚህ ተጽዕኖዎች ብዙዎቹ ከትምህርት ክፍለ ጊዜ ጋር በቀጥታ ከማይዛመዱ ተግባሮች የሚመጡ ናቸው። ስፖርት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ተቀጣጥሮ መጨዋወትና በቡድን መልክ ተሰባስቦ ጊዜ ማሳለፍ አደጋ ይፈጥራሉ። ሽማግሌው ትምህርት ቤት በተባለው ብሮሹር ከገጽ 22-5 ባሉት ሐሳቦች ተጠቅሞ ከትምህርት ሰዓት ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሚለው ርዕስ ሥር ያለውን ትምህርት ያወያያቸዋል። ወጣቶቹ በእነዚህ ነገሮች እንዲሳተፉ የሚገጥማቸውን ተጽዕኖ የሚጠቀሙ አስተያየቶችን ይሰጡና ለተለገሳቸው ምክር ያላቸውን አድናቆት ይገልጻሉ።
18 ደቂቃ፦ “ከመመሥከር ወደ ኋላ አላሉም።” ጥያቄና መልስ። ሁላችንም በአገልግሎት አንድ ዓይነት ሰዓት ልናሳልፍ ባንችልም ደስተኛ ሆነን በሙሉ ነፍሳችን ለማገልገል መጣር እንዳለብን አጉላ።
መዝሙር 34 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 191
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኅበሩ የጉባኤ መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ ካለ ጨምረህ አቅርብ።
12 ደቂቃ፦ “ትምህርት ቤት ሊከፈት ነው።” ጥያቄና መልስ። ልጆች በትምህርት ቤት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮችና ወላጆቻቸው እንዴት ሊረዷቸው እንደሚችሉ አጉላ።
11 ደቂቃ፦ “ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። በቀረበው ሐሳብ በመጠቀም አንድ ትዕይንት አዘጋጅተህ አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መምራት እንችላለንን?”በአገልግሎት የበላይ ተመልካች የሚቀርብ ንግግር። በኋላም በመከለስ ይደመደማል።
መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ሲያበረክቱና በእሱ ጥናት ሲያስጀምሩ ያገኟቸውን አጫጭር ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
20 ደቂቃ፦ “በአምላካዊ አስተዳደር ውስጥ ላለው ሥርዓት ተገዢ ከመሆን የሚመጡ ጥቅሞች።” አንድ ቤተሰብ አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት ከተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 2ን ይወያይበታል። መታዘዝን በሚያጎላ የማጠቃለያ አስተያየትም ውይይቱ ይደመደማል።
15 ደቂቃ፦ በጥቅምት ወር መጠበቂያ ግንብን እና ንቁ! ማበርከት። በዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ መጽሔቶቻችን ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እውነትን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰሙት በእነሱ አማካኝነት ነው። ሌላው ቀርቶ ሌሎች ጽሑፎች በሚበረከቱበትም ጊዜ እንኳን ከበር ወደ በር በሚደረገው የምሥክርነት ሥራ መጽሔቶቹን የማበርከትንና ያለማቋረጥ በእነሱ የመጠቀምን አስፈላጊነት አጉላ። መጽሔት ለማበርከት በሳምንት ውስጥ አንድ ቀን የመመደብን ጥቅም ጥቀስ። በመንገድ ላይና ከሱቅ ወደ ሱቅ መመሥከር ጽሑፍ ለማበርከት የሚከፍቱትን አጋጣሚዎች አብራራ። ወንድሞች የመጽሔት ደምበኛ ማግኘትን ግብ በማድረግ ያበረከቱለትን ሰው ስም እንዲመዘግቡ አሳስብ። ኮንትራት እንዲገቡ መጠየቅ እንደሚቻልም ግለጽ። ለአገልግሎት ከመውጣታችን በፊት ጥሩ ዝግጅት የማድረጉን ተፈላጊነት አጉላ። ሦስት አስፋፊዎች በተከታታይ አጫጭር መጽሔት የማበርከቻ ዘዴዎችን በትዕይንት እንዲያሳዩ አድርግ፤ ከመካከላቸው አንዱ ወጣት ይሁን።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።