የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/95 ገጽ 1
  • ክብራማ መብት የሆነው ስብከት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ክብራማ መብት የሆነው ስብከት
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአገልግሎት መብታችሁን እንደ ውድ ሀብት አድርጋችሁ ተመልከቱት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ ውድ መብት ነው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ለአገልግሎት ያለን ቅንዓት እንዳይቀዘቅዝ እንጠንቀቅ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ለአገልግሎት ያላችሁ ቅንዓት እንዳይቀዘቅዝ ጥረት አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 2/95 ገጽ 1

ክብራማ መብት የሆነው ስብከት

1 የምሥራቹ አገልጋይ መሆን ይሖዋ የሰጠን ክብራማ መብት ነው። (ሮሜ 15:16፤ 1 ጢሞ. 1:12) አንተ እንደዚህ አድርገህ ትመለከተዋለህን? የጊዜ ማለፍም ሆነ የሰዎች ትችት ለምሥራቹ አገልግሎት የምንሰጠውን ግምት እንዲቀንስብን ልንፈቅድ አይገባም። የአምላክን ስም መሸከም ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ክብር ነው። ለዚህ መብት ያለንን አድናቆት ከፍ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

2 የመንግሥቱን መልእክት መስበክ በዓለም ዘንድ ተወዳጅነትን አያተርፍልንም። ብዙዎች ለሥራችን የንቀትና የግዴለሽነት ስሜት ያሳያሉ። ሌሎች ይተቹታል እንዲሁም ይቃወሙታል። እንዲህ ዓይነቱ ተቃውሞ ከሥራ ባልደረቦች፣ ከጎረቤቶች ሌላው ቀርቶ ከቤተሰብ አባሎችም እንኳ ሊመጣ ይችላል። በእነሱ አመለካከት እንደ ተሳሳተና እንደ ሞኝ ሆነን ልንታይ እንችላለን። (ዮሐ. 15:19፤ 1 ቆሮ. 1:18, 21፤ 2 ጢሞ. 3:12) ተስፋ አስቆራጭ ትችቶቻቻው ቅንዓታችንን ለመቀነስና ቀዝቀዝ እንድንል ወይም ክብራማ መብታችንን እንድንተው ለማድረግ የታለሙ ናቸው። አሉታዊ አመለካከቶች የሚነዙት ‘የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፣ . . . የማያምኑትን አሳብ በሚያሳወረው’ በሰይጣን ነው። (2 ቆሮ. 4:4) ምን ምላሽ ትሰጣለህ?

3 ስለ መንግሥቱ የምናደርገው ስብከት በአሁኑ ወቅት ሁላችንም ልንሠራው ከምንችለው ሥራ ሁሉ የላቀ ሥራ መሆኑን በአእምሯችን መያዛችን በጣም አስፈላጊ ነው። በሌላ በምንም ዓይነት መንገድ የማይገኝ ሕይወት አድን መልእክት አለን። (ሮሜ 10:13–15) ዋናው ነገር በሰው ሳይሆን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ነው። ዓለም ስለ ስብከት ሥራችን ያለው አሉታዊ አመለካከት ምሥራቹን በድፍረት ከመናገር አያግደንም።— ሥራ 4:29

4 ኢየሱስ የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ ያገኘውን መብት ከፍተኛ ግምት ሰጥቶት ነበር። (ዮሐ. 4:34) ራሱን ምንም ሳይቆጥብ አገልግሏል እንዲሁም ሌሎች ነገሮች እንዲያባክኑት ወይም ተቃዋሚዎች እንዲያቀዘቅዙት አልፈቀደም። ዘወትር የመንግሥቱን መልእክት መስበክን በሕይወቱ ውስጥ አንደኛ ቦታ ይሰጠው ነበር። (ሉቃስ 4:43) የእሱን ምሳሌ እንድንኮርጅ ታዘናል። (1 ጴጥ. 2:21) ይህን ስናደርግ ‘ከአምላክ ጋር አብረን የምንሠራ’ ሆነን እናገለግላለን። (1 ቆሮ. 3:9) ከዚህ መብት የተሟላ ጥቅም እያገኘን ነውን? በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥራቹን ለሌሎች ለማካፈል የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን እንፈልጋለንን? የይሖዋ ምሥክሮች እንደ መሆናችን መጠን ዘወትር ‘ለስሙ ለመመስከር’ ዝግጁ መሆን አለብን።— ዕብ. 13:15

5 በአገልግሎት ያለን ተሳትፎ በአብዛኛው በአመለካከታችን ላይ የተመካ ነው። ይሖዋ ያደረገልንን ሁሉ በጥልቅ እናደንቃለንን? በአገልግሎቱ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ የሚገፋፋ ፍቅር በልባችን ውስጥ ለይሖዋ ኮትኩተናልን? አሁን ባገኘናቸውም ሆነ ወደፊት ይሖዋ ሊያደርግልን ቃል በገባልን ተስፋዎች ላይ ማሰላሰላችን ለፈጣሪ ያለን ፍቅር እንዲያድግ ያደርጋል። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ለድርጊት ያንቀሳቅሳል፤ ሁኔታችን በሚፈቅድልን መጠን በመንግሥቱ ስብከት ሥራ ያለማቋረጥ እንድንሳተፍና አዘውታሪ እንድንሆን ያደርገናል። ቅንዓታችን ለይሖዋና ለሰዎች ያለንን ፍቅር ያሳያል።— ማር. 12:30, 31

6 በምናደርገውና ስለ እሱ በምንናገረው ለአንድ ነገር ምን ያህል ግምት እንደምንሰጥ እናሳያለን። ስለ መንግሥቱ ለመስበክ ያገኘነውን መብት በእርግጥ ትልቅ ግምት እንሰጠዋለን? አገልግሎታችንን እናከብራለን? ተቃውሞ ሲያጋጥመንም እንኳ በዚህ ወሳኝ ሥራ ለመቀጠል ቆርጠናልን? ይህን አስደናቂ መብት ከፍ አድርገን ከተመለከትነው ቀናተኛ እንደምንሆንና በሙሉ ነፍሳችን እንደምናገለግል የተረጋገጠ ነው።— 2 ቆሮ. 4:1, 7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ