የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/95 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 2/95 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በየካቲትና በመጋቢት፦ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ይህ መጽሐፍ ከተበረከተ በኋላ ተመላልሶ መጠየቆች ሊደረጉ ይገባል፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመርም ጥረት መደረግ አለበት። በሚያዝያና በግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። በተደጋጋሚ በተሸፈኑ ክልሎች (ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች ከተባለው ብሮሹር በስተቀር) ማናቸውንም ብሮሹር መጠቀም ይቻላል። በተመላልሶ መጠየቆች ወቅት ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ኮንትራት እንዲገቡ መጠየቅ ይቻላል። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14–AM) መጠየቅ አለባቸው።

◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች እንቅስቀሴ መገምገም ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸውን የማሟላት ችግር ያለባቸው የዘወትር አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ አቅኚዎቹ እርዳታ የሚያገኙበትን ዝግጅት ማድረግ አለባቸው። አንዳንድ ሐሳቦችን ለማግኘት ማኅበሩ ጥቅምት 1, 1993 እና ጥቅምት 1, 1992 የላካቸውን ደብዳቤዎች (S–201–AM) ከልሱ። በተጨማሪም በ9–68 የመንግሥት አገልግሎታችን የመጽሔቱ አባሪ አንቀጽ 12–20 ተመልከቱ።

◼ የመታሰቢያው በዓል ዓርብ ሚያዝያ 14, 1995 ይከበራል። ምንም እንኳ ንግግሩ ቀደም ብሎ ሊጀምር ቢችልም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ግን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር መጀመር እንደሌለበት እባካችሁ አስታውሱ። በአካባቢያችሁ ፀሐይ የምትጠልቀው በስንት ሰዓት እንደሆነ ለማወቅ በአካባቢው ካሉ ምንጮች አረጋግጡ። ከመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ በስተቀር በዚያን ቀን ሌላ ስብሰባ አይኖርም። ጉባኤያችሁ ስብሰባ የሚያደርገው ዓርብ ከሆነና ክፍት የመንግሥት አዳራሽ የሚገኝ ከሆነ ስብሰባውን በሳምንቱ ውስጥ ለሌላ ቀን አዛውሩት።

◼ ሚያዝያ 23, 1995 ልዩ ንግግርና የመጠበቂያ ግንብ ጥናት ከተደረገ በኋላ አራት ገጽ ያለውን ልዩ መልእክት የያዘ ትራክት በብዛት በማሰራጨት የሚካሄደውን ልዩ ሥራ አስመልክቶ ማስታወቂያ ይነገራል። አስፋፊዎች ስላጋጠሟቸው ግራ የሚያጋቡ ችግሮች የሚጨነቁና አስተማማኝ መመሪያ ለማግኘት ለሚፈልጉ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ልዩ ትኩረት እንዲያደርጉ ማበረታቻ ይሰጣቸዋል። እያንዳንዱ አስፋፊ እንዲሁም በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት የመስክ አገልግሎት የሚጀምሩ አዲሶችም ጭምር ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግና ለዚህ ልዩ ዘመቻ አስተዋፅኦ ለማበርከት ይፈልጋሉ።

◼ በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ረዳት አቅኚዎች ሆነው ለማገልገል የሚፈልጉ አስፋፊዎች አሁኑኑ ዕቅድ ማውጣትና ቀደም ብለው ማመልከቻቸውን መስጠት ይኖርባቸዋል። ይህም ሽማግሌዎች ለመስክ አገልግሎት አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉና በቂ ጽሑፍ እንዲኖር ለማድርግ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። በሚያዝያ ወር ከአራት አስፋፊዎች አንዱ ረዳት አቅኚ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

◼ የተስተካከለ የቀን መቁጠሪያዎች ዋጋ:- ለሁሉም በ5 ብር። ጉባኤዎች ያሏቸውን የቀን መቁጠሪያዎች አስፋፊዎች እንዲወስዱት ልዩ ጥረት ሊያደርጉና ለዋጋ ልዩነቶች ቅናሽ ሊጠይቁ ይችላሉ። ጊዜያቸው ያለፉባቸው የቀን መቁጠሪያዎችም እንኳ ውብ የማስተማሪያ መርጃዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

◼ ክልል የሚለውን ቃል በአሁኑ ጊዜ ለብዙ ነገሮች እየተጠቀምንበት ስለሆነ የቃሉን አጠቃቀም ለመገደብ ቀጥሎ ያሉት ማስተካከያዎች ተደርገዋል:-

circuit—ወረዳ (በፊት ክልል ይባል የነበረው)

circuit overseer—የወረዳ የበላይ ተመልካች

circuit assembly—የወረዳ ስብሰባ

district—አውራጃ (በፊት ወረዳ ይባል የነበረው)

district overseer—የአውራጃ የበላይ ተመልካች

district convention—የአውራጃ ስብሰባ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ