የየካቲት የአገልግሎት ስብሰባዎች
የካቲት 6 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 19
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በቅርብ ጊዜ የወጡ መጽሔቶች ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እንዴት ሊበረከቱ እንደሚችሉ አሳይ።
17 ደቂቃ፦ “ክብራማ መብት የሆነው ስብከት።” ጥያቄና መልስ። በመጠበቂያ ግንብ 14–111 ገጽ 19 አንቀጽ 13–16 ላይ የተመሠረቱ ተጨማሪ ሐሳቦችን አቅርብ።
18 ደቂቃ፦ “ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስተዋወቅ።” ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ከገጽ 46–7 አንቀጽ 9–12 ያሉትን ሐሳቦች አክለህ ከአድማጮች ጋር ዋና ዋና ነጥቦችን ከልስ። በክልላችሁ ውስጥ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ምን ዓይነት መግቢያ እንደሆነ አብራራ። አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን በትዕይንት አሳይ። ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መጽሐፉን ማበርከት እንዳለብን ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። በቂ ትጥቅ ስላለን ከማበርከት ወደ ኋላ ማለት የለብንም።
መዝሙር 215 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 143
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። ማኅበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ ካለ ጥቀስ። “ተሻሽለው ከወጡት የሕዝብ ንግግሮች መጠቀም” የተባለውን ርዕስ በውይይት አቅርብ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
15 ደቂቃ፦ “የመንግሥቱን ቃል ትርጉም ማስተዋል።” ጥያቄና መልስ። ሁለት ወይም ሦስት ግለሰቦች እንዴትና መቼ የግል ጥናት እንዲሁም የዕለት ጥቅስ እንደሚያደርጉ እንዲናገሩ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “ለሌሎች አሳቢነትን አሳዩ— ክፍል 2።” በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግርና ውይይት። በጉባኤው ውስጥ የተስተዋሉ ማናቸውንም ችግሮች ጥቀስና ተገቢውን ምክር ስጥ።
መዝሙር 222 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 53
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በቅርቡ ከወጡ መጽሔቶች የተወሰዱ ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል የሚስማሙ ርዕሶችን ጠቁም።
23 ደቂቃ፦ “ከተሾሙ የበላይ ተመልካቾች ጥቅም ማግኘት።” አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 41 (ንዑስ ርዕስ) እስከ ገጽ 43 (ታችኛው ክፍል)፤ ከገጽ 45–6 (በግለሰብ ደረጃ መጠቀም) እስከሚለው ንዑስ ርዕስ ድረስ ያለው ክፍል በንግግር ይቀርባል። በተጨማሪም “የከተማ የበላይ ተመልካች” (ገጽ 46)፣ “የቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ” (ገጽ 53) እና “የዞን የበላይ ተመልካች”ን (ገጽ 53) አስመልክቶ አጠር ያለ ሐሳብ አቅርብ። ጥቂት የክለሳ ጥያቄዎችን አዘጋጅ።
17ደቂቃ፦ “ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ክትትል ማድረግ።” ከአድማጮች ጋር ተዋያይበት። ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አስመልክቶ ሰዎች የገለጿቸውን የአድናቆት አስተያየቶች ተናገር። (የግንቦት 15, 1986 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 እና የመጋቢት 1, 1987 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ተመልከት።) የተሰጡትን ሐሳቦች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ አንድ ወይም ሁለት አቀራረቦችን አዘጋጅ። ሁሉም ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ጥናት ለማስጀመር እንዲጥሩ አበረታታ።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
የካቲት 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጸሐፊው የመስክ አገልግሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሪፖርት እንዴት እንደሚሞላ ይጠቁማል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተብሎ ሪፖርት የሚደረገውንና በተመላልሶ መጠየቆች ውስጥ የሚካተተውንም ሆነ ጉባኤው የሚቸገርባቸውን ሌሎች ነገሮች ጥቀስ።
35 ደቂቃ፦ “ተስፋ የሌላቸው ሰዎች በሚያዝኑበት መንገድ አለማዘን።” በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት። አብዛኞቹን አንቀጾች ለማንበብ ሞክር።
መዝሙር 13 እና የመደምደሚያ ጸሎት።