ማስታወቂያዎች
◼ የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች በሚያዝያና በግንቦት:– መጠበቂያ ግንብና ንቁ! መጽሔቶች። በተደጋጋሚ በተሸፈኑ ክልሎች (ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች ከተባለው ብሮሹር በስተቀር) ማንኛውንም ብሮሹር መጠቀም ይቻላል። ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ኮንትራት እንዲገቡ መጋበዝ ይቻላል። በሰኔ፦ የቤተሰብህን ኑሮ አስደሳች አድርገው እና/ወይም ወጣትነትህ የተባሉት መጻሕፍት በልዩ የዋጋ ቅናሽ ማለትም በ3 ብር ይበረከታሉ። (ይህ የዋጋ ቅናሽ የሚሠራው ለሰኔ ወር ብቻ ነው።) በሐምሌና ነሐሴ፦ ከሚከተሉት ውስጥ ማንኛውንም ባለ 32 ገጽ ብሮሹር መጠቀም ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ፣ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” (እንግሊዝኛ)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? (እንግሊዝኛ) እና የምትወዱት ሰው ሲሞት (እንግሊዝኛ)። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14–AM) መጠየቅ አለባቸው።
◼ቀደም ሲል በማስታወቂያ እንደተነገረው ልዩ የዘመቻ ጽሑፍ የሆነው የመንግሥት ምሥራች እሑድ ሚያዝያ 23 በሚደረጉ የጉባኤ ስብሰባዎች እንዲሁም በዚያ ቀን በሚደረጉ የወረዳ ስብሰባዎችና የልዩ ስብሰባ ቀን ላይ ይወጣል። የአንዱ ትራክት ዋጋ 0.5 ሳንቲም (100ው 3 ብር) ነው። የመንግሥት ምሥራች እንደወጣ ወዲያውኑ ማከፋፈል ይጀመራል። ይህ ሁሉንም ጉባኤዎች፣ በትልልቅ ስብሰባዎች፣ በወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም በሌሎች እንቅስቃሴዎች ምክንያት የጉባኤ ፕሮግራማቸውን እንዲቀይሩ የተገደዱ ጉባኤዎችንም ጭምር ይመለከታል። ልዩ የሕዝብ ንግግሩን ከሚያዝያ 23 በኋላ የሚያደርጉ ጉባኤዎች የመንግሥት ምሥራችን ሚያዝያ 24 ማውጣታና ማሰራጨት ይችላሉ።
◼ገለልተኛ በሆኑ ቦታዎች የሚኖሩ አስፋፊዎች ‘ብርሃናቸውን ለማብራት’ በሚያደርጉት ጥረት ለማገዝ እንድንችል ለጉባኤዎች ባልተመደቡ ወይም በጉባኤዎች ሥር ባልሆኑ ገለልተኛ ክልሎች እያገለገሉ ያሉ አስፋፊዎችን አድራሻ ለማግኘት እንፈልጋለን።