የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/95 ገጽ 2
  • የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሚያዝያ 3 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 10 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 17 የሚጀምር ሳምንት
  • ሚያዝያ 24 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 4/95 ገጽ 2

የሚያዝያ የአገልግሎት ስብሰባዎች

ሚያዝያ 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 19

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። “ለመታሰቢያው በዓል የሚያስፈልጉትን ነገሮች አዘጋጁ” የሚለውን ከልስ።

15 ደቂቃ፦ “ስላሉን ነገሮች አመስጋኝ መሆን።” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን መግ 15–111 ገጽ 19–20 አንቀጽ 15–20 ላይ የተመሠረተ ተጨማሪ ሐሳብ አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ “መጠበቂያ ግንብና ንቁ! ላለንበት አጣዳፊ ጊዜ የሚሆኑ መጽሔቶች!” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት። ስለ መጽሔቶቹ የተሰጠውን አድናቆት የሚገልጽ ተሞክሮ አቅርብ። (የእንግሊዝኛ ንቁ! 91 7/22 ገጽ 9) ሁለት አስፋፊዎች በተሰጠው ሐሳብ ተመርኩዘው የአቀራረብ ዘዴ እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል ያሳዩ፤ ከዚያም የተነጋገሩበትን ሐሳብ እርስ በእርሳቸው በትዕይንት እንዲያሳዩ አድርግ።

መዝሙር 143 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 10 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 212

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ማኀበሩ የጉባኤው መዋጮ የደረሰው መሆኑን የገለጸበት ማስታወቂያ ካለ አንብብ። ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ የመርዳትን አስፈላጊነት ሁሉም እንዲገነዘቡ አድርግ። ሁሉም በዚህ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ በምናደርገው አገልግሎት ለመሳተፍ ልዩ ጥረት እንዲያደርጉ አጥብቀህ አሳስባቸው።

15 ደቂቃ፦ “መንግሥቲቱ ያስገኘችልንን አንድነት መጠበቅ።” ከአድማጮች ጋር ተወያይበት።

20 ደቂቃ፦ “የጌታ ሥራ የሚበዛላችሁ ሁኑ።” በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በጥያቄና መልስ የሚሸፈን። ልዩ የመንግሥት ምሥራች ን ለማዳረስ ከቤት ወደ ቤት ለሚደረገው አገልግሎት የተደረገውን ተጨማሪ ዝግጅት ጠቁም። ለጉባኤው የተመደበውን የአገልግሎት ክልል ለመሸፈን የተደረገውን እቅድ ተወያዩበት። ለመጀመሪያ ጊዜ አዲሶችም በዚህ አገልግሎት አንዲሳተፉ ለመርዳት ምን መደረግ እንዳለበት ግለጽ። (መጋቢት 1995 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 1 ተመልከት።)

መዝሙር 10 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 17 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 6

13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ስለ መታሰቢያው በዓል የሚያበረታቱ ጎላ ያሉ ሐሳቦችን እንዲሁም በበዓሉ ላይ ለተገኙት አዲሶች ተጨማሪ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ አመልክት። ሁሉም በሚያዝያ 23 በሚደረገው ልዩ የሕዝብ ንግግር ላይ እንዲገኙና ፍላጎት ያሳዩ አዲሶችም በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ እንዲረዷቸው አጥብቀህ አሳስብ። ለመንግሥት ምሥራች ስርጭት የተደረገውን የመስክ አገልግሎት ዝግጅት ግለጽ።

12 ደቂቃ፦ “የሚያስፈልግ ነገር እንዳለ ትመለከታለህን?” ጥያቄና መልስ። ሽማግሌዎች በእረኝነት ሥራቸው ሊፈጽሟቸው ያቀዷቸውን ግቦች በአጭሩ ግለጽ። በዚህ ረገድ እያንዳንዱ ግለሰብ ምን ድጋፍ ማበርከት እንደሚችል ግለጽ።

20 ደቂቃ፦ “ለመማር ፈቃደኛ የሆኑትን ፈልገህ አግኝ።” ተመላልሶ መጠየቅ የማድረግን አስፈላጊነት ተወያይበት። በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲጠቀሙ አበረታታ። አንድ ወይም ሁለት አጠር ያሉ አቀራረቦችን በትዕይንት አቅርብ።

መዝሙር 114 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሚያዝያ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 105

15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በክልሉ ውስጥ የመንግሥት ምሥራች ስርጭት ምን ያህል እየተሠራ እንዳለ ግለጽ። የመንግሥት ምሥራች በማሰራጨት የተሳካላቸው አስፋፊዎች ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። ለጉባኤው ክልል ተስማሚ የሆኑ መጽሔቶችን ለማበርከት የሚያስችሉ አቀራረቦችን ጠቁም። በምሽት ለሚደረግ ምሥክርነት ጉባኤው ያደረገው ዝግጅት ካለ አስታውቅ።

12 ደቂቃ፦ “የጥያቄ ሣጥን” ጥያቄና መልስ።

18 ደቂቃ፦ የቤተሰብ ጥናትህን ዘወትር መምራት። ባልና ሚስቱ የልጆቻቸው በመንፈሳዊ አለማደግ እንዳሳሰባቸው ይገልጻሉ። ባልየው የቤተሰብ ጥናትን በመምራት ረገድ ቸልተኛ እንደሆነ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ለቤተሰቡ የሚሆን ምንም ዓይነት መመሪያ ሳይሰጥ ብዙ ሳምንታት እንደሚያልፉ ይገልጻል። በትምህርት ቤት መምሪያ መጽሐፍ ገጽ 37–38 አንቀጽ 12–14 ላይ ያለውን ምክርና መመሪያ ይከልሳሉ። ሌላ ምንም ዓይነት ነገሮች ሳንካ እንዲሆንባቸው ሳይፈቅዱ በየሳምንቱ ለቤተሰብ ጥናት ቅድሚያ ለመስጠት ሁለቱም ይስማማሉ።

መዝሙር 187 እና የመደምደሚያ ጸሎት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ