ማስታወቂያዎች
◼ በሰኔ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- የቤተሰብ ኑሮ፣ ወጣትነትህ እያንዳንዳቸው በ3 ብር። በሐምሌና ነሐሴ፦ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ማንኛውንም መጠቀም ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ” (እንግሊዝኛ)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም (እንግሊዝኛ)፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴት ልታውቀው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ)፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት (እንግሊዝኛ) መስከረም፦ ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት መደረግ አለበት። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተዘረዘሩትን የዘመቻ ጽሑፎች ያላዘዙ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጻቸው (S-14- AM) መጠየቅ አለባቸው።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ ወይም እርሱ የወከለው ሰው ሰኔ 1 ወይም በተቻለ መጠን ከዚያ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤውን ሒሳብ መመርመር አለበት። ሒሳቡ ከተመረመረ በኋላ ለጉባኤው አስታውቁ።
◼ ከአሁን በኋላ ቤቴል የሚገኙት የጽሑፍ መላኪያና የሒሳብ ዲፓርትመንቶች የሚያስተናግዷችሁ ሰኞና ሐሙስ ይሆናል። ራቅ ካሉ ቦታዎች የሚመጡ ወንድሞች ግን በሌሎቹም ቀናት ሊስተናገዱ ይችላሉ።
◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች:- አማርኛ፦ ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር፣ የ4/94 (ተገዶ መደፈር) እና የ10/94 (ሞትን በገንዘብ መግዛት) ንቁ! መጽሔት። እነዚህ እትሞች እንደገና ታትመዋል። በድጋሚ ማዘዝ ትችላላችሁ። እንግሊዝኛ፦ የምትወዱት ሰው ሲሞት። ጣሊያንኛ፦ የ1995 የዓመት መጽሐፍ።
◼ በተጨማሪም በ12/94 መአ ላይ በማስታወቂያ የተገለጹት ጽሑፎች ዘግይተው አሁን ደርሰዋል። ከእነዚህ ጽሑፎች መካከል የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች የሆኑት የይሖዋ ምሥክሮች (እንግሊዝኛ)፣ “የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው?” የተባለው ብሮሹር (እንግሊዝኛ)፣ ውብ የሆነው የ1995 የቀን መቁጠሪያ በ5 ብር፣ የተለያዩ ዓይነት ካሴቶችና ሌሎች ብዙ የእንግሊዝኛና የፈረንሳይኛ ጽሑፎች ይገኙበታል።
◼ በሚከተሉት ቃላት ላይ የትርጉም ማስተካከያ ተደርጓል፦
Presiding overseer= ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች (ቀድሞ መሪ የበላይ ተመልካች ሲባል የነበረው።)
Theme= ጭብጥ (ቀድሞ አጠቃላይ መልእክት ሲባል የነበረው።)
Setting= መቼት (ቀድሞ አቀራረብ ሲባል የነበረው።)
Demonstration= ሠርቶ ማሳያ (ቀድሞ ትዕይንት ሲባል የነበረው።)
በዚህኛው መአ ከገጽ 3–6 ለቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የመምሪያ ንግግር የሚያገለግለው ክፍል ተተርጉሞ ቀርቧል። ሁላችሁም እንድትጠቀሙበት ሐሳብ እናቀርባለን።