የሰኔ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሰኔ 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 4
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። ከፊታችን ባሉት ቀናት የምናከናውናቸውን የሥራ እንቅስቃሴዎች ከልስ፤ በአገልግሎት በትጋት መሳተፋቸውን እንዲቀጥሉ፣ በስብሰባዎች እንዲገኙና ሪፖርት በወቅቱ እንዲመልሱ ሁሉንም አሳስባቸው።
15 ደቂቃ፦ “ይሖዋ ኃይል ይሰጣል።” ጥያቄና መልስ። በየካቲት 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 32 ላይ ያለውን ተሞክሮ አያይዘህ አቅርብ።
18 ደቂቃ፦ “ቤተሰቦችን ደስተኛ ለማድረግ የሚረዱ ዝግጅቶች።” ከአድማጮች ጋር ተወያዩበት። የተጠቀሱትን አቀራረቦች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። በሚያዝያና ግንቦት የተሰራጨውን የመንግሥት ዜና ያበረከትንላቸውን ሰዎች እንዴት ተመላልሶ መጠየቅ ልናደርግላቸው እንደምንችል ጥቂት አጠር ያሉ ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 172 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 12 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 105
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
17 ደቂቃ፦ “ክርስቶስ ለወጣቶች ምሳሌ ነው።” ጥያቄና መልስ። በመስከረም 1, 1986 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 4–6 ላይ ያለውን ሐሳብ ጨምረህ አቅርብ።
18 ደቂቃ፦ “ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ተመልሶ ማነጋገር አጣዳፊ ነው።” ጥያቄና መልስ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ብዙ አንቀጾችን ለማንበብ ሞክር።
መዝሙር 177 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 19 የሚጀምር ሳምንት
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በዚህ ሳምንት በመስክ አገልግሎት እንዴት መጽሔት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ወይም ሦስት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎችን አቅርብ።
22 ደቂቃ፦ ስብሰባዎቻችንን በቁም ነገር መመልከት። አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 77–80 ላይ የተመሠረተ ውይይት።
15 ደቂቃ፦ “ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት።” ጥያቄና መልስ። ቴሌቪዥን በመመልከት ስለሚጠፋው ጊዜ በግንቦት 22, 1991 የእንግሊዝኛ ንቁ! መጽሔት ገጽ 11 ላይ ባለው “ቴሌቪዥንን መቆጣጠር” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር የተሰጡትን ሐሳቦች ከልስ። ከዓለማዊ ዘመድና ጓደኛ ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፍም የሚያስከትለውን ጉዳት ጥቀስ።
መዝሙር 187 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 26 የሚጀምር ሳምንት
15 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ተመላልሶ የመጠየቅን አስፈላጊነት በአጭሩ ግለጽ። ዋነኛው የማስተማር ሥራችን የሚከናወነው የሰዎችን ፍላጎት ለመኮትኮት ተመልሰን በምንሄድበት ጊዜ ነው። በጽሑፎች ብቻ መንፈሳዊ እድገት ማድረግ የሚችሉ ሰዎች የሉም ማለት ይቻላል። ስለዚህ ተመልሰን ባለመሄዳችን እነርሱን ለመርዳት ያለንን ከሁሉ የተሻለ አጋጣሚ እናጣለን። ተመላልሶ መጠየቆች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ያስገኛሉ። ብዙ አስፋፊዎች ሳምንት ከመቆየት ይልቅ በአንድ ወይም በሁለት ቀናት ውስጥ ተመልሰው በመሄድ የተሻሉ ውጤቶች አግኝተዋል። የቀሩትን ጥቂት ደቂቃዎች ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀም።— አገልግሎታችን መጽሐፍ ከገጽ 88–9 ተመልከት።
15 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። የመጠበቂያ ግንብ ጥናት መሪ በጥያቄና መልስ ያቀርበዋል። በትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ ከገጽ 90–2 ላይ በመመርኮዝ ተጨማሪ ሐሳብ ስጥ።
15 ደቂቃ፦ በሐምሌ የሚበረከቱትን ጽሑፎች ከልስ። በጉባኤው እጅ የሚገኙ ብሮሹሮች ያሏቸውን ጎላ ያሉ ገጽታዎች ግለጽ። እነዚህን ብሮሹሮች ከቤት ወደ ቤት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል አስፋፊዎች በአጭሩ በሠርቶ ማሳያ እንዲያቀርቡ አድርግ። ምሳሌዎች:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? (ገጽ 26–7 አውጥተህ የተሰጡትን ምሳሌዎች አሳየውና ከተሰጡት ጥቅሶች በአንዱ በመጠቀም ወደፊት ስለምትመጣው ገነት ግለጽለት።) የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች (ገጽ 3 አንቀጽ 1 ወይም ገጽ 31 አንቀጽ 1 አውጣ።) በሥላሴ ማመን ይገባሃልን? (በገጽ 10 ላይ ያሉትን ሥዕሎች አሳየው፤ ወይም ደግሞ በገጽ 12 ላይ ያሉትን ርዕሶችና ንዑስ ርዕሶች አንብብለት።) የሙታን መናፍስት። (በገጽ 2, 12, 20 ወይም 21 ላይ ባሉት ሥዕሎችና በሥዕሎቹ መግለጫዎች ልትጠቀም ትችላለህ።) እንደ አንድ አካል ሆነው በዓለም ዙሪያ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉት የይሖዋ ምሥክሮች የተባለውን ብሮሹር ሁሉም ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸውና ፍላጎት ላሳዩ ዘመዶቻቸው እንዲያበረክቱ ልናበረታታቸው እንችላለን። በአሁኑ ጊዜ በእጅ ያሉት ብሮሹሮች የትኞቹ እንደሆኑ ለጉባኤው አሳውቅ።
መዝሙር 85 እና የመደምደሚያ ጸሎት።