የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/95 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
km 7/95 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ በሐምሌና በነሐሴ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ከሚከተሉት ውስጥ ማንኛውንም ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች መጠቀም ይቻላል:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ “እነሆ! ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ” (እንግሊዝኛ)፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም (እንግሊዝኛ)፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን ታመጣለች፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው? እንዴት ልታውቀው ትችላለህ? (እንግሊዝኛ) እና የምትወዱት ሰው ሲሞት (እንግሊዝኛ)። መስከረም፦ ለዘላለም መኖር በተባለው መጽሐፍ የምንጠቀም ሲሆን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ለማስጀመር ጥረት መደረግ አለበት። ጥቅምት፦ ንቁ! ወይም መጠበቂያ ግንብ ኮንትራት ማስገባት። የመጽሔቶቹን ቅጂዎች ለማበርከት ልዩ ጥረት አድርጉ። ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱትን የዘመቻ ጽሑፎች እስካሁን ያልጠየቁ ጉባኤዎች በቀጣዩ ወር የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S–14–AM) መጠየቅ አለባቸው።

◼ ማንኛውም አስፋፊ የራሱን ወይም ኮንትራት ያስገባቸውን ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች ኮንትራት የሚመለከት ችግር ካጋጠመው ይህንን ለጉባኤው ጸሐፊ ማመልከት አለበት፤ ጸሐፊው ችግሩን ለቅርንጫፍ ቢሮው ያስታውቃል። ለእንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ ደብዳቤ ሲጻፍ ከደብዳቤው ጋር መጀመሪያ ኮንትራቱ የተሞላበትን ቅጽ ፎቶ ኮፒ ከደብዳቤው ጋር አያይዞ መላክ ወይም ቢያንስ ስሙን፣ አድራሻውን፣ ቀኑን፣ ቋንቋውን፣ የትኛው መጽሔት እንደሆነና ኮንትራቱ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እንደገና ጽፎ መላክ ጥቅም አለው። እባካችሁ የኮንትራቱን ቅጽ ወደ ቢሮ ከላካችሁ በኋላ ጥያቄ ከማቅረባችሁ በፊት ቢያንስ ሦስት ወር ጠብቁ።

◼ በአሁኑ ጊዜ በየዓመቱ ለጉባኤ የሚላኩት ቅጾች ለእያንዳንዱ ጉባኤ እየተላኩ ነው። የተጠየቀው ገንዘብ ከጉባኤው ሒሳብ ወጪ ተደርጎ ወዲያውኑ መከፈል አለበት (የሚከፈለው ከጽሑፍ ሒሳብ አይደለም)። ተጨማሪ ቅጾች የሚያስፈልጉ ከሆነ የጽሑፍ መጠየቂያ ቅጽ በሆነው S–14–AM ማዘዝ ይቻላል። ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ እነዚህ ቅጾች በሥርዓት መቀመጣቸውንና ለሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ወንድሞች በተገቢው መንገድ መሠራጨታቸውን መከታተል አለበት።

◼ ሠርግን በተመለከተ ለሁሉም የሽማግሌ አካላት የተላከው የግንቦት 15, 1989 ደብዳቤ ቅጂ በእጃችሁ መኖሩን ለማረጋገጥ የጉባኤ ጸሐፊዎች በጠቅላላ የጉባኤውን ፋይሎች እንድትመረምሩ እንጠይቃችኋለን። በፋይሉ ውስጥ ምንም ቅጂ ከሌለ በጋብቻ ሥነ ሥርዓት ወቅት ሥርዓታማ መመሪያዎችን መከተል እንዲቻል እባካችሁ አንድ ፎቶ ኮፒ ከማኅበሩ ጠይቁ።

◼ በእጃችን ያሉ አዳዲስ ጽሑፎች:-

አማርኛ፦ “መንግሥትህ ትምጣ”፤ በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት። ትግሪኛ፦ ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት። (ትራክት ቁ.–15)፤ ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን? (ትራክት ቁ.–19)፤ ለተጨነቁት ሰዎች የሚሆን ማጽናኛ። (ትራክት ቁ.–20)፤ በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት። (ትራክት ቁ.–21)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ