የሐምሌ የአገልግሎት ስብሰባዎች
ሐምሌ 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በተጨማሪም የሚያማምሩ ሥዕላዊ መግለጫዎች የያዘው የ1995 የቀን መቁጠሪያ ሁሉም አድማጮች እንዳላቸውና እንደሌላቸው ጠይቅ። ከሌላቸው በጽሑፍ አገልጋዩ በኩል አሁኑኑ እንዲያዙ ልታበረታታቸው ትችላለህ። የአንዱ ዋጋ 5 ብር ነው።
17 ደቂቃ፦ “ነቅታችሁ ጠብቁ።” በጥያቄና መልስ።
18 ደቂቃ፦ “ስታገለግሉ በተለያዩ ብሮሹሮች ተጠቀሙ።” በተሰጡት አቀራረቦች ከአድማጮች ጋር ተወያይባቸው። በብሮሹሮቹ ላይ ያሉትን ትኩረት የሚስቡ ገጽታዎች በተመለከተ አጠር ያለ ሐሳብ ስጥ። ብሮሹሮቹን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሁለት ወይም ሦስት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 10 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 155
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
15 ደቂቃ፦ “የይሖዋ ማሳሰቢያዎች በመንፈሳዊ እያነቃቁን ነውን?” በጥያቄና መልስ።
20 ደቂቃ፦ “የምሥራቹ አገልጋዮች።” በአገልግሎታችን መጽሐፍ ከገጽ 81–88 ላይ የተመሠረተ ንግግር። እባክህ ጉባኤያችሁ ከቤት ወደ ቤት የሚደረገውን አገልግሎት ምን ያህል መደበኛ የአገልግሎቱ ክፍል እንዳደረገው ግለጽ።
መዝሙር 79 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 105
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ፦ “ብሮሹር ላበረከታችሁላቸው ሁሉ ተመላልሶ መጠየቅ አድርጉላቸው።” ይህንን ክፍል እንዲያቀርብ የተመደበው ወንድም ፍላጎት ያሳዩትንና ጽሑፍ የወሰዱትን ሁሉንም ሰዎች ተከታትሎ መርዳት አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ከሌሎች ሦስት አስፋፊዎች ጋር ይወያያል። በሰኔ የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጣው “ፍላጎት ያሳዩትን ሰዎች ተመልሶ ማነጋገር አጣዳፊ ነው” ከሚለው ርዕስ አንዳንድ ዋና ዋና ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ። በተጨማሪም በአገልግሎታችን መጽሐፍ ከገጽ 88–89 ያሉትን ትምህርቶች አቅርብ። የተሰጡትን አቀራረቦች ይመረምራሉ፤ እንዲሁም አቀራረቦቹን በአገልግሎታቸው እንዴት ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ አንዳቸው ለሌላው ያሳያሉ።
15 ደቂቃ፦የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት። እድገት የሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በሚመራ ሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር የበለጠ ጥረት እንዲያደርጉ አበረታታ። አገልግሎታችንን ለመፈጸም መደራጀት በተባለው መጽሐፍ ገጽ 90, 91 ላይ የቀረቡትን ሐሳቦች ግለጽ። ከዚህ በተጨማሪ ከጉባኤው የተገኙ ተሞክሮዎችን አጠር አድርጎ መናገር ይቻላል።
መዝሙር 47 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 215
5 ደቂቃ፦የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
12 ደቂቃ፦ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። ወይም በነሐሴ 1, 1994 የእንግሊዝኛ መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 27–30 ላይ የተመሠረተ “ለአረጋውያን ክርስቲያናዊ ፍቅር ማሳየት” የሚል ንግግር አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ ሰው ምን ይለኛል? በሚያዝያ 1, 1974 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 201–3 ላይ የተመሠረተ ንግግርና ሠርቶ ማሳያ። ብዙውን ጊዜ ዓለማዊ በሆኑ ጎረቤቶቻችን ተጽዕኖ የሚደርስብን ለምን እንደሆነ የሚያሳይ ንግግር አቅርብ። (ገጽ 201ን እንዲሁም ገጽ 202 ላይ ያለውን የመጀመሪያ አንቀጽ ሸፍን።) ከዚያም ተሞክሮ ያላቸው ባልና ሚስት ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናታቸውን በሚቃወሙ ዓለማዊ ጎረቤቶቻቸው ሳቢያ ፍራቻ ካደረባቸው በቅርቡ ለእውነት ፍላጎት ካሳዩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ሲያጠኑ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ አቅርብ። (የቀሩትን በርዕሱ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ነጥቦች ጥቀስ።) በቅርቡ ፍላጎት ያሳየ ቤተሰብ ተስፋ መቁረጥና መሸነፍ የሌለበት ለምን እንደሆነ የሚያሳዩ ምክንያቶችን ጠበቅ አድርገህ ግለጽ።
13 ደቂቃ፦“ብቃት ያላቸውና ሁለገብ የሆኑ አገልጋዮች።” አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 91–94 በጥያቄና መልስ የሚደረግ ውይይት። የመጀመሪያውንና የመጨረሻውን ንዑስ ርዕስ አጠር አድርገህ አቅርበው፤ ይሖዋ በጥሩ ሁኔታ በማስታጠቅ ለሰጠን ነገሮች አድናቂ የመሆንን አስፈላጊነት በማጉላት “በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች መጠቀም” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ጊዜ ወስደህ ሰፋ አድርገህ አቅርበው። በየወሩ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው መጽሔቶችን ለማበርከትና በየወሩ ከምናበረክታቸው ጽሑፎች አንድ ወይም ከዚያ በላይ ቅጂዎችን ለማበርከት ሁሉም የግል ግብ ቢኖራቸው ጥሩ ይሆናል። በዚህ ወር ባገኘናቸው አመቺ አጋጣሚዎች ሁሉ የተለያዩ ብሮሹሮችን በማበርከት ረገድ አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ መጣር አለብን።
መዝሙር 33 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 31 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 136
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
15 ደቂቃ፦ “የምታንጹ ሁኑ።” በአንድ ሽማግሌ የሚቀርብ ውይይትና ንግግር።
20 ደቂቃ፦ በነሐሴ የሚበረከቱትን ጽሑፎች ግለጽ። በዚህ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹሮች ጥቀስ። በሐምሌ ወር ብሮሹሮችን ሲያበረክቱ ያገኟቸውን ማንኛውንም አስደሳች ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አስፋፊዎችን ጠይቅ። አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? በተባለው ብሮሹር በመጠቀም እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል አሳይ። በክፍል 1 የመጀመሪያ አንቀጽ ውስጥ የቀረበውን ጥያቄ ጠይቅ። የቤቱ ባለቤት ከአንቀጽ 2–4 ላይ ስለተሰጡት ሐሳቦች ምን እንደተሰማው እንዲገልጽ አድርግ። ብሮሹሩ አምላክ በእርግጥ እንደሚያስብልንና ወደፊት በሚመጣው የአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ ከመከራ ነፃ የሆነ ሕይወት ማግኘት እንደምንችል እንደሚያሳይ ንገረው። ሌላ ጊዜ ተገናኝታችሁ ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ እንድትችሉ ሐሳብ አቅርብለት።
መዝሙር 177 እና የመደምደሚያ ጸሎት።